የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ለትግራይ ክልል ከ67 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የምግብና የመድኃኒት ድጋፍ አደረገ

8 Mons Ago 432
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ለትግራይ ክልል ከ67 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የምግብና የመድኃኒት ድጋፍ አደረገ

ድጋፉን የጠቅላይ ም/ቤቱ ፕሬዚዳንት ሼኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ አስረክበዋል።

ለወገን ደራሽ ወገን መሆኑን የጠቅላይ ም/ቤቱ ፕሬዚዳንት ሼኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተናግረዋል።

"አንድነታችንን እና ፍቅራችንን ለመግለፅ በክልሉ ለተቸገሩ ወገኖች የሚውል ድጋፍ ይዘን መጥተናል፤ በቀጣይም በምንችለው ሁሉ ትብብር ለማድረግ ዝግጁ ነን" ብለዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ፥ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ከቀናት በፊት በተደረገው ይቅርታ እና እርቅ መሰረት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤትን የሰላም ጥሪ ተቀብሏል።

ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋን ጨምሮ 70 የሚጠጉ አባላት ያሉት የልዑካን ቡድን ትናንት መቐለ ገብቷል።

የልዑካን ቡድኑ መቐለ አሉላ አባነጋ አየር ማረፊያ ሲደርስም፤ የትግራይ እስልምና ጉዳዩች ም/ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ አደም አብዱልቃድርን ጨምሮ ከትግራይ ከሁሉም አካባቢዎች የተወጣጡ የሙስሊም ማህበረሰብ ተወካዮች አቀባበል አድርገውለታል።

የልዑካን ቡድኑ በቆይታው በመቐለ የሚገኘውን የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ እና አል ነጃሺ መስጂድን ጎብኝቷል።

በደሐብ ያሲን


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top