ኮሚሽኑ በእስያ፣ አውስትራሊያና ኒውዚላንድ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያየ

10 Mons Ago 198
ኮሚሽኑ በእስያ፣ አውስትራሊያና ኒውዚላንድ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያየ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በዛሬው ዕለት በእስያ፣ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር የበይነ መረብ ስብሰባ አድርጓል።

በውይይት መድረኩ ላይ እንደከዚህ ቀደሙ ኮሚሽኑ ራሱን በማስተዋወቅ ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ውስጥ ሊኖራቸው ስለሚገባ ተሳትፎ እና ሊያደርጉት ስለሚገባ ድጋፍ ውይይት ተደርርጓል።

በመርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙ የኮሚሽኑ አባላት ኮሚሽኑን እና የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል።

በዚህም ስለ ሀገራዊ ምክክር መሰረታዊ ፅንሰ-ሀሳብ፣ ሀገራዊ ምክክር ለኢትዮጵያ ስላለው ፋይዳ፣ በኮሚሽኑ ስለተከናወኑ አንኳር ተግባራት እና ኮሚሽኑ ስለሚገዛባቸው የሕግ ማዕቀፎች ማብራሪያ መቅረቡን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ገለፃውን ተከትሎ ውይይቶች የተደረጉ ሲሆን፤ ኮሚሽኑ በእስያ፣ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በትብብር ስለሚሰራባቸው መንገዶች የተለያዩ ምክረ-ሀሳቦች ቀርበዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ኮሚሽኑ በአሰራር ሂደቱ ላይ ሊያስብባቸው የሚገቡ እና አቅጣጫ ጠቋሚ የሆኑ ጉዳዮች ተነስተዋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top