የጅቡቲ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ነገ በሚካሄደው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ጉባዔ ላይ ንግግር ያደርጋሉ

10 Mons Ago 374
የጅቡቲ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ነገ በሚካሄደው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ጉባዔ ላይ ንግግር ያደርጋሉ

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባዔ ነገ ይካሄዳል። 

በጉባዔው ላይ የጅቡቲ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ድልኤታ መሀመድ ድልኤታ ንግግር እንደሚያደርጉ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። 

የጅቡቲ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ድልኤታ መሀመድ ድልኤታ የተመራው የጅቡቲ ፓርላማ የልዑካን ቡድን አዲስ አበባ የገባው ትናንት ነው። 

የኢፊዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ በቦሌ አየር ማረፊያ ተገኝተው ለልዑካን ቡድኑ አባላት አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን፤ ዛሬ ረፋድ ላይም በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል። 

የልዑካን ቡድኑ አባላት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ ተገኝተው ከአቶ ታገሰ ጫፎ እና ከኢትዮ-ጅቡቲ የወዳጅነት ቡድን ጋር ከተወያዩ በኋላ፤ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት የተለያዩ የሥራ ክፍሎችን ጎብኝተዋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top