ሀገራዊ ችግሮች ላይ በጋራ በመወያየትና የጋራ መፍትሄ በማስቀመጥ ዘላቂ ሰላምና ልማት ማምጣት ይገባል -  የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎች

1 Yr Ago 429
ሀገራዊ ችግሮች ላይ በጋራ በመወያየትና የጋራ መፍትሄ በማስቀመጥ ዘላቂ ሰላምና ልማት ማምጣት ይገባል -  የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎች

 

ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በአሶሳ ከተማ ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር  ተወያይቷል፡፡

በአጀንዳ ልየታና በተሳታፊ መረጣ ላይ ባተኮረው መድረክ የሀይማኖት አባቶች፣ የሴት አደረጃጀቶች፣ የሙያ ማህበራት፣ ልዩ ትኩረት የሚሹ ዜጎች ተወካዮች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡ 

ኮሚሽኑ እያካሄደ ያለው የቅድመ ዝግጅት ስራና በቀጣይ የሚያካሂደው ሀገራዊ ውይይት በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ያስችላል ሲሉ የመድረኩ ተሳታፊዎች ገልጸዋል ፡፡

የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ብሌን ገ/መድህን ኮሚሽኑ በዚህ ዓመት አጋማሽ ለሚያካሂደው  ሀገራዊ የምክክር መድረክ የአጀንዳ መረጣና የተሳታፊ ልየታ ስራዎችን በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች  እያከናወነ መሆኑን በመድረኩ ላይ ገልፀጸዋል፡፡

በጀማል አህመድ


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top