በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና ከመስከረም 29 ጀምሮ ይሰጣል፡-የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች አገልግሎት

1 Yr Ago 199
በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና ከመስከረም 29 ጀምሮ ይሰጣል፡-የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች አገልግሎት
በትግራይ ክልል በ2012 ዓ.ም በፀጥታ ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከመስከረም 29 ቀን ጀምሮ በሶስት ዙር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል፡፡
 
አገልግሎቱ በክልሉ የሚሰጠውን ፈተና አስመልክቶ ከፌደራል ፖሊስ ኃላፊዎችና ከክልሉ የፈተና አስፈጻሚዎች ጋር ምክክር ማድረጉን ነው ገለጸው፡፡
 
የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ይልቃል ወንድሜነህ በክልሉ ተቋርጦ የቆየውን የ12ኛ ክፍል ፈተና ለማስቀጠል በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
 
ም/ዋና ዳይሬክተርሩ ፈተናውን በሶስት ዙር ለመስጠት መታቀዱን ጠቁመው፤ የ2012 ዓ.ም የመጀመሪያው ዙር ፈተና ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡
 
የተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ ከመስከረም 8 እስከ 12 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት የሚከናወን መሆኑን የፈተና አስተዳደር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ወንዶሰን እየሱስወረቅ ጠቁመዋል፡፡
 
የትምህርት ምዘናና ምርምር ስራዎች እና የብሔራዊ ፈተና አዘገጃጀት ሰነዶች ቀርበው ሰፊ ምክክር እንተደረገባቸው ከአገልግሎቱ ተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top