የብርክስ ቡድን ባንክ አባል ለመሆን ከጠየቁ 15 ሀገራት የ5ቱ ተቀባይነት ሊኖረው እንደሚችል ተገለጸ

1 Yr Ago 1558
የብርክስ ቡድን ባንክ አባል ለመሆን ከጠየቁ 15 ሀገራት የ5ቱ ተቀባይነት ሊኖረው እንደሚችል ተገለጸ

አዲሱ የልማት ባንክ ከ15 ሀገራት የቀረበለትን የአባልነት ጥያቄ እያጤነው እንደሆነ የቀድሞ የብራዚል ፕሬዚዳንት እና የባለብዙ ወገን አለም አቀፍ አበዳሪ ድርጅት መሪ ዲልማ ሮሱፍ ገልጸዋል፡፡

ዲልማ ሮሱፍ ከፋይናንሻል ታይምስ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ በመጀመሪያ ዙር ከ4 እስከ 5 ሀገራት ጥያቄ ተቀባይነት እንደሚያገኝ ጠቅሰዋል፡፡

ባንኩ በብዙ መልክአ ምድራዊ እና ብዝሃነትን በሚያስተናግድ መልኩ ተደራሽ ለማድርግ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

በቅርቡ ከ8 እስከ 10 ቢሊዮን ዶላር ድረስ ለማበደር እና ከዚህ ውስጥ 30 በመቶውን በአባል ሀገራቱ ምንዛሬ ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

በዶላር ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ እና ባለብዙ ዋልታ የፋይናንስ ሲስተም ለመዘርጋት በመጀመሪያ ዙር በደቡብ አፍሪካ እና በብራዚል የገንዘብ ምንዛሬ ለማበደር ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡

ባንኩ ለደቡብ አፍሪካ በራንድ ፤ ለብራዚል በሪል እንዲሁም ለህንድ በሩፒ እንደሚያበድር ገልጸው፤ ሬንምንቢ በተባለው የቻይና ምንዛሬ ማበደር ቀድሞውኑ መጀመሩን መግለጻቸውን የዘገበው አር ቲ ነው፡፡

ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ሕንድ፣ ቻይናን እና ደቡብ አፍሪካን ያቀፈው የብሪክስ ቡድን ፤ ለመሠረተ ልማት እና ዘላቂ እድገት ፕሮጀክቶች የገንዘብ ድጋፍ ለመስጠት በ2014 አለም አቀፉን ልማት ባንክ አስጀምረዋል።

ባንኩ ለቢዝነስ በይፋ ኢ.ኤ.አ 2015 የተከፈተ ሲሆን ባግላዴሽ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ግብጽ እና ኡራጋይ ተቀላቅለዋል፡፡  

ባንኩ እንደ አይ ሜ ኤፍ እና የዓለም ባንክ ያሉ በአሜሪካ ተፅዕኖ ስር ካሉ የገንዘብ ተቋማት አማራጭ እንዲሆን የተቋቋመ ነው።

 


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top