ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ለምታደርገው ጥረት ዓለም አቀፉ ማኀበረሰብ ድጋፍ ማድረግ አለበት - ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀሥላሴ

1 Day Ago 78
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ለምታደርገው ጥረት ዓለም አቀፉ ማኀበረሰብ ድጋፍ ማድረግ አለበት - ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀሥላሴ

የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እና ለመከላከል ኢትዮጵያ እያከናወነቻቸው ለምትገኘው የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ እና መሰል ፕሮጀክቶች ዓለምአቀፉ ማኀበረሰብ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባው ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀሥላሴ ገለጹ፡፡

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀሥላሴ በአዘርባጃን ባኩ እየተካሄደ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 29) ላይ ንግግር አድርገዋል።  

ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭን ጨምሮ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እና እንክብካቤ ላይ እያከናወነቻቸው ስለሉ ዋና ዋና ተግባራት አስረድተዋል።

በተጨማሪም እንዲህ አይነት መሰል ጥረቶች እንዲጎለብቱ ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top