ኢትዮጵያ እና ሀንጋሪ በኢኮኖሚ መስክ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ተስማሙ

1 Mon Ago 220
ኢትዮጵያ እና ሀንጋሪ በኢኮኖሚ መስክ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ተስማሙ

ኢትዮጵያ እና ሀንጋሪ በኢኮኖሚ መስክ ያላቸውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር ተስማምተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ ከሀንጋሪ አምባሳደር አቲላ ቶማስ ካፕኒይ ጋር የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በሚያጠናክሩ በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን ግንኙነቶች ዙሪያ በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ሀንጋሪ ለኢትዮጵያውያን ነጻ የትምህርት ዕድል በመስጠት ያበረከተችውን አስተዋፅኦ አድንቀዋል።

በቀጣይም የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በኢኮኖሚ መስክ የበለጠ መጠናከር እንዳለበት ገልጸው፤ የሀንጋሪ ኩባንያዎች በማምረቻ፣ በግብርና እና ማዕድን ዘርፎች በኢትዮጵያ እንዲሠማሩ ጠይቀዋል።

በኢትዮጵያ የሀንጋሪ አምባሳደር አቲላ ቶማስ በበኩላቸው፤ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የዲፕሎማሲ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።

ሀንጋሪ ከኢትዮጵያ ጋር በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በአቅም ግንባታ እና በሰብዓዊ ድጋፍ ያላትን ግንኙነት የበለጠ አጠናክራ ትቀጥላለች ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top