አፍሪካ በዓለም የኢኮኖሚ ልዕለ ኃያል መሆን የሚያስችላት የሰው ኃይል እና የተፈጥሮ ሀብት እንዳላት የወቅቱ የህብረቱ ሊቀመንበር እና የኮሞሮስ ፕሬዝዳንት አዛሊ አሶውማኒ ገለጹ፡፡

1 Yr Ago
አፍሪካ በዓለም የኢኮኖሚ ልዕለ ኃያል መሆን የሚያስችላት የሰው ኃይል እና የተፈጥሮ ሀብት እንዳላት የወቅቱ የህብረቱ ሊቀመንበር እና የኮሞሮስ ፕሬዝዳንት አዛሊ አሶውማኒ ገለጹ፡፡
በኅብረቱ አዳራሽ እየተከበረ ባለው የአፍሪካ ቀንና የአፍሪካ ህብረት 60ኛ አመት በዓል አዛሊ አሶውማኒ ንግግር አድርገዋል፡፡
አዛሊ አሶውማኒ አፍሪካ በራስ መተማመንን ለመመለስ እና ለመገንባት ማናቸውንም ጥረት በሁሉም መስክ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸው፤ ያሉንን ሃብቶች በመጠቀም የአባቶቻችንን ህልም ማሳካት አለብን ብለዋል፡፡
ቀደምት አባቶች በዚህ ታሪካዊ ቀን ሁለት ግቦችን ለማሳከት አቅደው፤ ቅኝ ግዛትንና አፓርታይድን ታግለው በማስወገድ ግባቸውን ማሳካታቸውን ገልጸዋል፡፡
ባለፉት 6 አስርት አመታት ያሳካናቸው ብዙ ግቦችን አጠናክረን ማስቀጠል እና ከስህተቶቻችን ተምረን ለቀጣይ ትውልድ የተሻለች አህጉር የማስረከብ ግዴታ አለብን ብለዋል፡፡
የአጋርነት እና አንድነት ችቦአችንን ከፍ አድርገን ለማብራት ያሉብንን የሰላም እና ዴሞክራሲ ችግሮች መፍታት አለብን ብለዋል፡፡
በንግግራቸውም በጦርነት ላይ ያሉት የሱዳናውያን ወደ ሰላማዊ ድርድር እና ምክክር እንዲመለሱ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት አፍሪካ በከኮቪድ እና በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ምክንያት በኢኮኖሚ እና ግሽበት ችግር ውስጥ መሆኗን የጠቀሱት ልቀመንበሩ፤ ድህነት እና በድህነት አማካይነት እየተከሰተ ያለውን ሽብርተኝነት መታገል እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡
አዛሊ አሶውማኒ ሁሉም የአፍሪካ ሀገራት በቅንጅት እና በተባበረ ክንድ የተቀመተውን አጀንዳ 2063 እና የዘላቂ ልማትና ሰላም ግብ በማሳከት አፍሪካ በአለም አቀፍ መድረክ የሚገባትን ተደማጭነት አንድታገኝ ማድረግ እንችላለን ብለዋል፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top