የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት አባላት መቐለ ገቡ

1 ዓመት በፊት 659
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት አባላት መቐለ ገቡ
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት አገር በቀል እና የውጭ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በማስተባበር ወደ ትግራይ ተጉዟል።
የምክር ቤቱ አባላት በመቐለ አሉላ አባነጋ ኤርፖርት ሲደርሱ የትግራይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት ተቋም አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት አባላት በትግራይ ያለው የሰብዓዊ፣ መልሶ ግንባታና መልሶ ማቋቋም ጉዳዮችን በተመለከተ በትግራይ ካሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ኢ.ፕ.ድ ዘግቧል።

ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top