በጌዴኦ ዞን ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ 16 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

1 Day Ago 91
በጌዴኦ ዞን ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ 16 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ
በጌዴኦ ዞን ባለፈው አንድ ወር ውስጥ በንቅናቄ በተሰራ ሥራ ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ 16 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን የዞኑ የሕዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ገልጿል።
 
በዞኑ ህብረተሰቡ በቦንድ ግዥ በነቂስ በመሳተፍ ዳግም አሻራውን እያኖረ መሆኑም ተመላክቷል።
 
የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ሮቤ እንደገለጹት፤ የሕዳሴው ግድብ ዋንጫ ወደዞኑ መምጣትን ተከትሎ ባለፈው አንድ ወር ውስጥ የገቢ ማሰባሰብ ሥራ የተከናወነ ሲሆን16 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቦ ከ11 ሚሊዮን ብር በላይም ቃል መገባቱን ገልጸዋል።
 
በድጋፉ ከመንግስት ሠራተኛውና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተጨማሪ ተቋማትና ማህበራትም መሳተፋቸውን አመልክተዋል።
 
የዞኑ ህዝብ በቦንድ ግዥ በነቂስ በመሳተፍ ዳግም አሻራውን ማኖሩንም አቶ ብርሃኑ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
 
የሕዳሴው ግድብ ዋንጫ በዞኑ የነበረውን የአንድ ወር ቆይታ አጠናቆ ለወላይታ ዞን መሰጠቱን ያነሱት አቶ ብርሃኑ፤ በበጀት ዓመቱ ቀጣይ ወራት ለግድቡ የሚሰበሰበውን ገቢ 60 ሚሊዮን ብር ለማድረስ ታቅዷል ብለዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top