ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ልምድ መቅሰም እንደምትፈልግ ገለፀች

1 Day Ago 51
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ልምድ መቅሰም እንደምትፈልግ ገለፀች

የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የግብርና ሚኒስትር ግሪጎር ሙታሻል ጋር ሁለቱ ሀገራት በግብርናው ዘርፍ በጋራ መስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡  

የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) አፍሪካ ለግብርና ልማት ምቹ የተፈጥሮ ሃብት እንዳላት ጠቅሰው፤ ነገር ግን የአፍሪካ ሃገራት ህዝባቸውን በአግባቡ መመገብ እንዳልቻሉ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ አያይዘውም፤ ይህንን ችግር ለመቅረፍ የኢትዮጵያ መንግስት ለግብርናው ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡

የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የግብርና ሚኒስትር ግሪጎር ሙታሻል በበኩላቸው፤ በግብርናው ዘርፍ በኢትዮጵያ ለመጣው ለውጥ እውቅና ሰጥተው፤ የሃገሪቱ መንግስትም ከኢትዮጵያ ልምድ መቅሰም እንደሚፈልግ ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በግብርናው ዘርፍ ልምድ ለማካፈል ያላትን ፍቃደኝነት የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በቀጣይ በጋራ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተባብሮ ለመስራት ከመግባባት መድረሳቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡  


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top