በግብርናው ዘርፍ የሚመራው የሴፍቲኔት ፕሮግራም ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረገ ነው፦ የግብርና ሚኒስቴር

1 Mon Ago 178
በግብርናው ዘርፍ የሚመራው የሴፍቲኔት ፕሮግራም ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረገ ነው፦ የግብርና ሚኒስቴር
በግብርናው ዘርፍ የሚመራው የሴፍቲኔት ፕሮግራም ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
 
ሚኒስትሩ በግብርናው ዘርፍ ለሚመራው የሴፍቲኔት ፕሮግራም ዘላቂ የኑሮ መሰረት ለሆኑ ጉዳዮች በዘንድሮው ዓመት 80 ቢሊዮን ብር በሆነ በጀት ድጋፍ መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡
 
ዜጎች ከእርዳታ እና ከተረጂነት እንዲወጡ እንደሀገር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡
 
በግብርናው ዘርፍ ምርት እና ምርታማነት እንዲጨምርና ዜጎች በምግብ እራሳቸውን እንዲችሉ የሴፍቲኔት ድጋፍ እና የግብርና ግብዓት ድጎማ ከፍ ማለቱንም ጠቁመዋል፡፡
 
ወደ አርሶ አደሩ የሚደርሰው የማዳበሪያ መጠን እንዳይቀንስም 53 ቢሊዮን ብር ድጎማ ተደርጓል ብለዋል፡፡
 
ባለፉት 5 ዓመታት ኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ካደረገችባቸው ዘርፎች መካከል የግብናው ዘርፍ ተጠቃሽ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
 
እንደ ሀገር የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ የሀገርን ሉዓላዊነት ማስከበር ቁልፍ መሆኑ ታምኖበትም እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
 
ኢትዮጵያ በምግብ እራሷን እንድትችል በግብርናው ዘርፈ ባከናወነችው በርካታ ተግባራት በተባበሩት መንግስታት የምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) መሸለሟ ይታወሳል፡፡
 
በሜሮን ንብረት

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top