በቅርቡ ሥራ የጀመረው ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ከትናንት ጀምሮ ምርቱን ለገበያ እያቀረበ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ፋብሪካው የማምረት ሥራውን በፍጥነት እንዲጀምር የተደረገው ምርቱን በቶሎ ወደ ገበያ በማቅረብ በሀገር ደረጃ ያለውን የሲሚንቶ ገበያ ለማረጋጋትና እንደሀገር የተጣለበትን ከፍተኛ ኃላፊነት ለመወጣት መሆኑ ተገልጿል፡፡
ፋብሪካው ምርቱ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ከግብዓት ምርት ጀምሮ ዘመናዊና የተደራጀ ላቦራቶሪ ገንብቶ ባለሙያ መድቦ በብቃት እየሠራ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ምርቱ ከሚመለከተው አካል የጥራት መስፈርት ያሟላ መሆኑንም ከፋብሪካው ያገኘነው መረጃ አመልክቷል፡፡