በአማራ ክልል "ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም" በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ከተሞች የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የሰላም ኮንፈረንሱ በክልሉ በገጠሙት የፀጥታ ችግሮች ዙሪያ የሚመክር መሆኑ ተመላክቷል።
ኮንፈረንሱ በጎንደር፣ ደባርቅ፣ በአይከል፣ በፈንድቃ፣ በወሎ እና በሌሎች ከተሞች እየተካሄደ ሲሆን የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት፣ የዞን እና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
የሰላም ኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች በወቅታዊ ሰላምና ፀጥታ ዙሪያ ውይይት እያካሄዱ እንደሚገኙም ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡