የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን
ጥቅምት 23 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ይህ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ነው!
ይህ ድምፅ ኢትዮጵያን እየተረከ ስድሳ ዓመታት ሆነ። እነሆ ዛሬ የኢትዮጵያ የበኩር ድምፅ ስድሳ ዓመታት ሆነው። ስድሳ የጋራ ትዝታ ዓመታት። ስድሳ የሀገር ግንባታ ዓመታት። ስድሳ የሀገር ባሕል መስኮትነት። ስድሳ የትምህርት ዓመታት። ስድሳ የጥበብ መድረክነት ዓመታት። የኢትዮጵያ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማኅበራዊ ዐበይት ሁነቶች እና መታጠፊያዎች የተበሰሩባቸው ስድሳ ዓመታት።
በልጅነትም በወላጅነትም የየቤቶቻችን የጋራ የመረጃ እና የመዝናኛ ምንጭ የሆነው የኛው የሀገር መስኮት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከተመሰረተ ዛሬ ስድሳ ዓመት ሆነው።
ክቡራን ኢትዮጵያውያን የእናንተው ለሆነው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ስድሳኛ ዓመት እንኳን አደረሳቸሁ እያልን፤ በዚህ ታሪካዊ ቀን የበለጠ ልናገለግላቸሁ መዘጋጀታችንን እንገልፅላችኋለን። በአዳዲስ የይዘት ለውጦች ፍላጎታችሁን እና የውድ ሀገራችንን ፍላጎት እና ህልም ለማሟላት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ እንገኛለን። አግዙን። የኢትዮጵያ መተረኪያ መስኮት እንዲሆን እየለወጥነው እንገኛለን።
ተመልከቱን!
እንኳን አደረሳችሁ።
ለኢትዮጵያ ልዕልና