በ3ኛ ዙር ወደ ሀገር ለሚገቡ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን አቀባበል እየተደረገ ነው

2 Days Ago
በ3ኛ ዙር ወደ ሀገር ለሚገቡ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን አቀባበል እየተደረገ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ታኅሳስ 13 ቀን 2016 ዓ.ም በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገር ቤት እንዲመጡ ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ 3ኛው ዙር ሁለተኛ ትውልድ ኢትጵያዊያን ወደ ሀገር ቤት እየገቡ ይገኛል፡፡

በዚህም በዛሬው ዕለት በ3ኛ ዙር ወደ ሀገር ለሚገቡ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ይፋዊ የአቀባበል ስነ-ስርዓት በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት መካሄድ ጀምሯል፡፡

በአቀባበል ስነ-ስርዓቱ ላይ የሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ጥሪ ብሔራዊ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እንዲሁም የሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ጥሪ ብሔራዊ ኮሚቴ አስተባባሪና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይነህ አቅናውን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

የሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ጥሪ ብሔራዊ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤ ጥሪውን ተከትሎ ባለፉት ሁለት ዙሮች ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው በመምጣት ከታሪካቸውና ባህላቸው ጋር በሚያስተሳስሯቸው ልዩ ልዩ ተግባራት ላይ መሳተፋቸውን ገልጸዋል።

በሶስተኛውና የማጠቃለያው ምዕራፍ ላይ ለሚሳተፉ ተጓዦችም የዕረፍት ጊዜያቸውን የሚያጣጥሙባቸውና አሻራቸውን የሚያሳርፉባቸው በርካታ ተግባራት መሰናዳታቸውን ጠቅሰዋል። 

በዛሬው ዕለት አቀባበል ከተደረገላቸው ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መካከል በሐረሪ ክልል በሚከበረው 26ኛው ‘የሐረር ቀን’ ላይ ለመሳተፍ የመጡ ተጓዦች እንደሚገኙበት ጠቅሰው፣ በመላው ዓለም የሚኖሩ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያንም  ወደ ሀገራቸው በመምጣት ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

በዛሬው ዕለት ከአውስትራሊያና ከአሜሪካ ለመጡ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ይፋዊ አቀባበል የተደረገ ሲሆን፣ በቀጣይ ጊዜያትም አቀባበሉ የሚቀጥል መሆኑን ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top