በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም እና ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን መሪነት የዋዜማው ሥርዓት ቀጥሏል።
በቀጣይ ዓመታት ተረኞች የሆኑት የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን እና የሲኤምሲ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት በቀኝ እና በግራ ንሽውን ተቀብለዋል።




ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራት እና ገዳማት የተውጣጡ ሊቃውንት አብረው እያመሰግኑ እንደሚገኙ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን ያገኘነው መረጃ ያመለከታል።