የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ ላይ ለተነሡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ ዋና ዋና ነጥቦች

10 Days Ago 1393
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ ላይ ለተነሡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ ዋና ዋና ነጥቦች

 የኤርትራ ሚናን በተመለከተ፦

• ትግራይ ውስጥ በሚፈጠር ትርምስ እናተርፋለን የሚሉ በርካታ ናቸው፤ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ የኤርትራ መንግሥት ነው።

• ትግራይን ከካርታ ላይ የማጥፋት ሒደትን ያስቆመው የፕሪቶሪያ ስምምነት ነው። ይህ ደግሞ የኤርትራ መንግሥትን ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር አኮራርፏል።

• ኤርትራ የኢትዮጵያ መንግሥት ይወርረናል ብሎ ሲያስብ ትግራይን እንደ ማቀዠቀዣ ይጠቀማል፤ ትንሽ ጉልበት ሲሰማው ደግሞ ከትግራይ ጥቂት ቡድኖች ጋር ሆኖ ለመረበሽ ይሠራል።

• አንድ የትግራይ ጄኔራል ከኤርትራ መንግሥት ጋር ይህንን ሥራ ሲሠራ ማየት እጅግ የሚገርም ነገር ነው፤ ምክንያቱም ከኤርትራ ጋር የሚሠራ ቡድን ለትግራይ ሕዝብ ደንታ የለውም።

• በክልሉ ለተፈጠረው ቀውስ የኤርትራ መንግሥት አስተዋፅኦ አለው፤ ክልላለችን የጦር ቀጣና ለማድረግ እየሠራ ነው።

በትግራይ በተፈጠረው ሁኔታ የፌዴራል ዝምታን በተመለከተ፦

• በትግራይ ክልል የተፈጠረው ነገር የህወሓት ግጭት ነው፤ ፕሬዚዳንቱን አውርጃለሁ የሚሉ ወገኖች አሉ። ከንቲባ እኛ ነን የምንሾመው የሚሉ አሉ። ማሕተም ነጥቆ በጀት የሚገባው ለኔ ነው የሚል ወገን አለ። በአንድ በኩል የፌዴራል መንግሥት ማድረግ የሚጠበቅብህን አላደረግህም እያለ እኔን ይወቅሰኛል። አንዳንዱ የፌዴራል መንግሥት ለምን ዝም አለ? ብሎ ይወቅሳል። ይዋጣላቸው ብሎ ይሆን?

• ከጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ ከሌሎች የፌዴራል መንግሥት አመራሮች ጋር ስናወራ “ትግራይ ላይ አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነት ላለማድረግ ወስኗል” የሚል መልስ ይሰጡኛል።

• ነገር ግን አሁን ካለው ሁኔታ አንፃር ዝም ማለት የለበትም። የትግራይን ድንበር መጠበቅ አለበት። አሁን በተፈጠረው ቀውስ ዝም ማለት ትክልል አይደለም።

ትግራይ ጦርነት ማስተናገድ አትችልም፦

• አሁን ላይ ትግራይ ጦርነት ማስተናገድ አይችልም፤ ወጣቱ የእገሌን ወንበር ለማዳን ብሎ ጦርነት አይገባም። የትግራይ ወጣቶች ሊዋጉ የሚችሉት የውጭ ኃይል ሲወርራቸው ብቻ ነው። የትግራይ ሕዝብ በፍፁም ጦርነት መሸከም አይችልም።

• ሰላምን ለማፅናት ከፌዴራል መንግሥት ጋር በቅርበት ከመሥራት ውጪ ምንም አማራጭ የለንም።

• ረብሻው እየፈጠሩ ያሉ ጥቂት ኃይሎች “ማን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በእጅጉ ርቋል?” የሚለው ላይ በማተኮር እየሠሩ ነው።

• ከፌዴራል መንግሥቱ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለኝም በማለት ተቀባይነት ለማግኘት የሚሠሩ አሉ።

• ይህ ቡድን ያልተረዳው አዲስ አበባ ሔደህ ክብራችንን አስነካህ የሚል የትግራይ ሕዝብ አለመኖሩን ነው።

• በአጠቃላይ ግጭትን ለማስቀረት ግጭቱን የሚጀምሩ ሰዎች “ይህ ነገር የሚያስከትለው ጥፋት አለ” ብለው ማሰብ አለባቸው።

በትግራይ ክልል መፈንቅለ መንግሥት ተካሂዷል ወይ ለሚለው፦

• አሁን እየተደረገ ያለው መፈንቅለ መንግሥት ነው፤ ማሕተም የሚነጠቀው ለምንድን ነው? ሥልጣን ሳይኖረው መሬት የሚሸነሽን ኃይል አለ። በተግባር የመፈንቅለ መንግሥት ሥራ እየተሠራ ነው።

ወርቅ እና የሰዎች ዝውውር፦

• የወርቅ እና የሰዎች ዝውውር በጣም በሰለፊው እየተካሄደ ነው፤ አሁን ሰላምን የማወክ ሥራ የሚሠሩ ሰዎች በዚህ ላይ የተሰማሩ ናቸው። የወርቅ እና የሰው ዝውውር ላይ የሚሰማሩ ሰዎች ሰላም ቢፈልጉ ነው የሚገርመው።

የታጠቁ ኃይሎችን በተመለከተ፦

• ትግራይ ሀገር ናት ብለው የሚያስቡ በርካቶች ናቸው፤ ያንን ማሰብ ይችላሉ። ግን እውነታውን ማወቅ አለብን። ሀገር መሆን ስለተመኘን ብቻ ሊሆን አይችልም። ያለውን እውነታ ተቀብሎ የትግራይ ኅልውና እንዲጠበቅ መሥራት አለብን።

• ግን ታጣቂዎች ረበሹ የሚለው ነገር ባያስኬድም፤ አመራር የሆኑት ግን ሥልጣን ስለሚፈልጉ ረብሻውን መፍጠራቸው አልቀረም።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top