ትራምፕ የፈለጉትን ማዕድን ሊያገኙ ነው? ዩክሬን በውድ ማዕድኖቿ ዙሪያ ከአሜሪካ ጋር ትመክራለች፦ ፕሬዝዳነት ዘለንስኪ

10 Days Ago 237
ትራምፕ የፈለጉትን ማዕድን ሊያገኙ ነው? ዩክሬን በውድ ማዕድኖቿ ዙሪያ ከአሜሪካ ጋር ትመክራለች፦ ፕሬዝዳነት ዘለንስኪ
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ጋር እንደከዚህ ቀደሙ ድጋፍ ብቻ ሳይሆን ሃብትሽን አካፍይን ጥያቄም ገጥሟቸዋል።
 
ፕሪዝዳንት ትራምፕ አሜሪካ ላደረገችው ድጋፍ ዩክሬን ደግሞ ከውድ ማዕድናቷ ልታካፍለን ይገባል ማለታቸው የሰሞኑ የሚዲያ መነጋገሪያ ሆኗል።
 
ይህ ጉዳይ ፕሬዝዳንት ትራምን እና ፕሬዝዳንት ዘለንስኪን በቃላት ሲያነጋገር ቆይቶ አሁን ዩክሬን የአሜሪካ ፍላጎት ለመቀበል ወስናለች እየተባለ ነው።
 
በፕሬዝዳንት ትራምፕ ሀሳብ ላይ ፈፅሞ አልስማማም ሲሉ የነበሩት ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ አሁን ላይ በአሜሪካ ሀሳብ እንደሚስማሙ እና ከአሜሪካ ጋር በማዕድን ዘርፍ በጋራ ለመስራት እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል።
 
ዩክሬን በዋና አጋሯ አሜሪካ ሀሳብ አልስማማም ማለቷ ከአሜሪካ የምታገኛቸው በተለይ የጦር መሳሪያ ድጋፍ እንዲቆም መደረጉ ወደ ስምምነቱ ለመምጣት ሳያስችል እንዳልቀረ ነው የተገልጸው።
 
እንዲሁም የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከሩሲያ መንግስት ጋር ለመስራት በማቀዱ ስጋት የገባው የዘለንስኪ አስተዳደር፤ የቀረበው የማዕድን ዘርፍ ልማት ስምምነት ላይ ይሁንታውን አሳይቷል ነው የተባለው።
 
በእነዚህ ጉዳዩች ለመምከር እና የሻከረው የሁለቱ ሀገራት ግኑኝነት ላይ ለመወያየት ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ወደ አሜሪካ ያቀናሉ ተብሎም ይጠበቃል።
 
ሩሲያ በቁጥጥሯ ሥራ ባሉት ግዛቶች በማዕድን ዘርፍ ከአሜሪካ ጋር መስራት እንደምትፈልግ መግለጿ ዩክሬን በፍጥነት ሃሳቧን እንድትቀይር ሳያደርጋት እንዳልቀረም ነው የተዘገበው።
 
ዩክሬን ያላት የማዕድን ሀብት 15 ትሪሊዮን ዶላር የሚገመት ሲሆን 350 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ማዕድን መገኛ ቦታ ደግሞ በሩሲያ ቁጥጥር ስር ውስጥ ነው።
 
በሀብተሚካኤል ክፍሉ
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top