አሽከርካሪዎችን እና እግረኞችን የሚያስቀጡ የመንገድ ትራፊክ ደንብ ጥሰቶች የትኞቹ ናቸው?

7 Hrs Ago 513
አሽከርካሪዎችን እና እግረኞችን የሚያስቀጡ የመንገድ ትራፊክ ደንብ ጥሰቶች የትኞቹ ናቸው?

ተሻሽሎ በፀደቀው የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 557/2016) አሽከርካሪዎችን እና እግረኞችን የሚያስቀጡ የመንገድ ትራፊክ ደንብ ጥሰቶችን ምን ያህል የውቃሉ?

 እግረኞችን 100 ብር የሚያስቀጡ ጥሰቶች

  1. ተገቢውን ጥንቃቄ ሳያደርግ መንገድ ማቋረጥ
  2. ለተሽከርካሪ የተፈቀደ መንገድ ላይ ያለበቂ ምክንያት የቆመ ወይም የተጓዘ
  3. ለእግረኛ መንገድ ተብሎ ከተከለከለ መንገድ ውጭ የተጓዘ

እግረኞችን 150 ብር የሚያስቀጡ ጥሰቶች

  1. በብረትም ሆነ በግንብ ተለይተው የታጠሩ መንገዶች ዘሎ መንገድ ያቋረጠ
  2. በጆሮ ማዳመጫ የተለያዩ ድምፅችን እያዳመጠ መንገድ ያቋረጠ
  3. ለእግረኛ ክልክል ነው የሚል ባለበት መንገድ ወይም እግረኛ እንዳያቋርጥ በተከለከለበት የማሳለጫ ወይም ቀለበት መንገድ ያቋረጠ

ከላይ የተዘረዘሩ ጥፋቶች አንዱን ፈፅሞ ክፍያ መፈፀም ያልቻለ ወይም ያልፈለገ ማናኛውም ሰው ተመጣጣኝ የማኅበራዊ አገልግሎት እንዲሰጥ ይደረጋል።

 አሸከርካሪዎችን 500 ብር የሚያስቀጡ የ1ኛ ደረጃ ጥሰቶች

  1. ተሸከርካሪ ያለአግባብ የጎተተ
  2. የግጭት መከላከያ ቆብ(ሄልሜት) ሳያደርግ ወይም አድርጎ ሳያስር ብስክሌት የነዳ ወይም ብስክሌቱን መሪ በእጅ ሳይዝ የነዳ
  3. በተሸርካሪው ውስጥ የተሟላየመጀመሪያ ዕርዳታ መስጫ ኪት እና የሚሠራ የድገተኛ እሳት ማጥፊያ መሳሪያ ሳይኖረው የንግድ ተሸከርካሪ ያሽከረከረ
  4. የሚበኑ ወይም የሚበተኑ ነገሮችን ያለአግባብ ጭኖ ያሽከረከረ
  5. ጭነትን እያፈሰሰ ወይምበመስቀለኛ መንገድ ላይ በልመና ለተሰማሩ ሰዎች ገንዘብ የሰጠ ወይም ግብይት ያደረገ
  6. በትራፊክ መብራት ላይ ወይምበመስቀለኛ መንገድ ላይ በልመና ለተሰማሩ ሰዎች ገንዘብ የሰጠ ወይም ግብይት ያደረገ
  7. ሲጋራ እያጨሰ ያሽከረከረ
  8. የአደጋ ጊዜ አገልግሎትተሸከርካሪን የአደጋ አገልግሎት ሥራ ላይ ሳይሆን አለአግባብ የተፈቀደለትን የድምፅና የአደጋ ምልክት መብራት በመጠቀም ያሽከረከረ
  9. ከ13 ዓመት በታች የሆነንሕፃን ከአሽከርካሪው ጎን በሚገኘው የተሸከርካሪው ክፍል (ጋቢና) ውስጥ አስምጦ ያሽከረከረ
  10. ለጉዳት ተጋላጭ ለሆኑ የመንገድ ተጠቃሚዎች ተገቢውን የድጋፍና ጥንቃቄ ሳያደርግ ያሽከረከረ አሽከርካሪ

አሸከርካሪዎችን 1000 ብር የሚያስቀጡ የ2ኛ ደረጃ ጥሰቶች

  1. የተሟላ የጭነት ማቀፊያ (ስፖንዳ) ሳይኖረው ጭነት ጭኖ የሽከረከረ
  2. የጥሩምባ ድምፅ ያለአግባብ ወይም በተከለከለ ቦታ ላይ የተጠቀመ ወይም ተገቢ ባልሆነ የማስጠንቀቂያ (የጥሩምባ) ድምፅ የተጠቀመ
  3. በመንገድ ላይ ተሸከርካሪ ያጠበ ወይም እንዲታጠብ ያደረገ
  4. በአውቶቡስ ማቆሚያ ስፍራ ላይ፣ እግረኛ መንገድ ላይ ትራፊክ ምልክት ወይም መብራት አጠገብ፣ በተሸከርካሪ መግቢያ ወይም መውጫ በር ላይ ሌላ ተሸከርካሪ ደርቦ ወይም በመንገድ ምልክት አመካኝነት ማቆም በተከለከለበት ማናቸውም ስፍራ ላይ ተሸከርካሪ ያቆመ
  5. የአሽከርካሪውን ዕይታ የሚከለክል መጋረጃ፣ ተለጣፊ ለስቲክ ወይም ሌሎች ተመሳሳይ ነገሮችን በተሸከርካሪው ላይ ያስቀመጠ ወይም የለጠፈ
  6. በተፈቀደው ፍጥነት በታች ያሽከረከረ ወይም ቀኙን ጠርዝ ሳይዝ በዝግታ ያሽከረከረ
  7. ከመጠን በላይ ድምፅ እያሰማ ወይም በጆሮ ማዳመጫ እያዳመጠ ያሽከረከረ
  8. የአሽከርካሪ ማረጋገጫ ፈቃድ ኖሮት ሳይዝ ያሽከረከረ ወይም የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃዱን ሳያድስ ያሽከረከረ
  9. በሕግ በተፈቀደው ርቀት ምልክት ሳያሳይ የተጠመዘዘ፤ አቅጣጫ የቀየረ፤ ተሸከርካሪ የቀደመ ወይም ተሸከርካሪ ያቆመ
  10. በመንገድ ላይ ያለን ውኃ በተሽከርካሪው አማካኝነት በእግረኛ ላይ እንዲረጭ ያደረገ
  11. የትራፊክ ምልክት  ወደ ቀኝ ብቻ መታጠፍ በሚፈቅድ መንገድ ላይ የዘጋ
  12. በተከለከለ መንገድ ላይ ወይም በየመንገዱን ቀኝ ዳር ሳይዝ ተሳፋሪ ወይም ዕቃ የጫነ ወይም ያወረደ
  13. የማብሪያ ጊዜ መብራት እያለው ሳያበራ ያሽከረከረ
  14. በጠባብ መንገድ ላይ ወይም በመታጠፊያ መንገድ በ12 ሜትር ውስጥ ተሸከርካሪ ያቆመ
  15. ለእግረኛ ወይም ተላላፊ ቅድሚያ ያልሰጠ
  16. ቅድሚያ መስጠት ላለበት ተሸከርካሪ ቅድሚያ ያልሰጠ
  17. በትራፊክ ደሴት ላይ ያሽከረከረ ወይም የመንገድ አከፋፋይ ደሴትን (መስመርን) በማቋረጥ ያሽከረከረ
  18. ከተፈቀደለት ጊዜ በላይ የተበላሸ ተሽከርካሪን መንገድ ላይ ያቆመ ወይም አቁሞ የጠገነ
  19. የሚታጠፍበት አቅጣጫ ሳይዝ ወይም ደርቦ የታጠፈ
  20. ሁለት መስመር ባለው መንገድ ላይ በቀኝ በኩል ተሸከርካሪ የቀደመ
  21. ምልክት ሳያሳይ ተሸከርካሪ ያቆመ ወይም ከቆመበት ቦታ ያንቀሳቀሰ
  22. ለአደጋ አገልግሎት ተሽከርካሪ ቅድሚያ ያልሰጠ
  23. ወደ ማይሄድበት አቅጣጫ ምልክት ያሳየ
  24. ከሚገባው በላይ ጭስ እያጨሰ ወይም ዘይት ወይም ነዳጅ እያፈሰሰ የሚሄድ ተሸከርካሪን ያሽከረከረ
  25. ከ7 ዓመት በታች የሆነ ሕፃንን ለደኅንነቱ ሲባል በተሠራው ማቀፊያ ውስጥ ሳያስቀምጥ ያሽከረከረ
  26. የትራፊክ ተቆጣጣሪ ትዕዛዝ ያልፈፀመ ወይም የተሳሳተ መረጃ የሰጠ ወይም እንዲቆም ሲታዘዝ በእምቢተኝነት ሳይቆም የሄደ
  27. በተራፊ ጭነት ላይ ተገቢውን ምልክት ሳያደርግ ወይም በተሸከርካሪው ላይ የተጫነውን ጭነት በሚገባ ሳያሥር ወይም ሳይሸፍን ያሽከረከረ
  28. በእግረኛ ማቋረጫ መንገድ ላይ ወይም ከእግረኛ ማቋረጫ ከ12 ሜትር ውስጥ ተሸከርካሪ ያቆመ
  29. የእሳት አደጋ ተሸከርካሪ ውኃ መሙያ ቦታ ላይ ወይም በእሳት አደጋ መከላከያ እና በሆስፒታል መግቢያ እና መውጫ በር ላይ ተሸከርካሪ ያቆመ
  30. ባልተፈቀደ ቦታ ወይም ባልተወሰነ ሰዓት ወይም የለማጅ ምልክት ሳይለጠፍ አሽርካሪ ማሽረከር ያስተማረ ወይም ያለማመደ
  31. የተሸከርካሪው በር ተከፍቶ እያለ ወይም ጨርሶ ሳይዘጋ ያሽከረከረ
  32. የአሽከርካሪው ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ኖሮት የሚያሽከረክረውን ተሸከርካሪ ፈቃድ ለሌለው ወይም በዚህ ደንብ ሰመረት ለታገደበት ሰው አሳልፎ የሰጠ
  33. ተሸከርካሪው በእንቅስቃሴ ላይ እያለ ተሳፋሪ ጫነ ወይም ያወረደ
  34. ባለ ሦስት ጎን አንፃባራቂ ምልክት በበቂ ርቀት ሳያስቀምጥ የተበላሸ ተሸርካሪ ያቆመ
  35. ከተፈቀደለት ጊዜ በላይ በማዘግየት ተሸከርካሪን በመንገድ ላይ ያቆመ
  36. ተሸከርካሪውን ያለአግባብ ወደ ኋላ ያሽከረከረ
  37. በአደጋ ጊዜ አገልግሎት ተሸከርካሪ በ100 ሜትር ርቀት ተከትሎ ያሽከረከረ
  38. በተሸከርካሪ ማቆሚያ ስፍራ ወይም በመንገድ ላይ ተሸከርካሪ የጠገነ

 አሸከርካሪዎችን 1500 ብር የሚያስቀጡ የ3ኛ ደረጃ ጥሰቶች

  1. የጉዞ ረድፍን ወይም መስመሩን ሳይጠብቅ ያሽከረከረ
  2. የሕዝብ ማመላለሻ ተሽርካሪ ሞተር እየሠራና በተሸከርካሪው ውስጥ መንገደኞች እያሉ ነዳጅ መሙላት
  3. ከተሸከርካሪው የመጫን አቅም በላይ ትርፍ ሰው የጫነ
  4. በምድቡ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ኖሮት ከተፈቀደለት ደረጃ በላይ ተሸከራካሪን ያሽከረከረ
  5. ተንቀሳቃሽ ስልክ በእጅ ይዞ እያነጋገረ ወይም መልእክት እየፃፋ እየላከ ወይም እያነበበ ያሽከረከረ
  6. የጭንቅላት መካላከያ (ሄልሜት) ሳያደርግ ወይም አድርጎ ሳያስር ወይም አብሮት የጫነው ሰው ማድረጉንና ማሰሩን ሳያረጋግጥ ሞተር ሳይክል ያሽከረከረ
  7. በጭነት ተሸከርካሪ በሕግ ከተፈቀደለት ውጪ ሰውን ያሳፈረ
  8. በማብሪያ ጊዜ መብራት ሣይኖረው የሽከረከረ
  9. ቴሌቪዥን ወይም ሌሎች ምስሎችን ተሸከርካሪ ውስጥ እየጸመለከተ ያሽከረከረ
  10. የደኅንነት ቀበቶ ሳያስር ወይም ተሳፋሪዎችን ቀበቶ ማሠራቸውን ሳያረጋግጥ ያሽከረከረ
  11. ቀይ የትራፊክ መብራት የጣሰ
  12. በተከለከለ መንገድ ወይም አቅጣጫ ያሽከረከረ
  13. በትራፊክ ክብ ደሴትን በግራ ያቋረጠ
  14. በድልድይ ላይ ተሸካርካሪ ያቆመ
  15. ጫት ቅሞ ወይም እየቃመ ወይም አደንዛዥ ዕፅ ወስዶ ያሽከረከረ
  16. በመስቀለኛ መንገድ ላይ ቅድሚያ ሊሰጠው ለሚገባ ተሸከርካሪ ቅድሚያ ያልሰጠ
  17. በሕግ ከተፈቀደው ከፍታ ርዝመት እና ስፋት ውጭ ጭነት የጫነ
  18. የመለያ ሰሌዳ ቁጥሩ ሊታይ የማይችል ቦታ ላይ ያሰረ ወይም የተደመሰሰ ወይም የተቆረጠ ወይም የተሸፈነ ወይም የተለያዩ ቀለማትን የቀባ ተሸከርካሪን ያሽከረከረ
  19. ተላላፊ ሠሌዳ ከተፈቀደለት ጊዜና ቦታ ውጪ የተጠቀመ
  20. ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ጭነትን ከሕዝብ ጋር የጫነ
  21. ለአውቶብስ ብቻ ተብሎ የተለየ መንገድ ላይ ያሽከረከረ
  22. በተሽከርካሪው የውጭ አካል ላይ ሰው የጫነ
  23. ከተሽከርካሪው የመጫን አቅም በላይ ትርፍ ሰው የጫነ1500 ብር እና በጫነው በእንዳንዱ ትርፍ ለተጫነ ሰው ተጨማሪ 100 ብር ይቀጣል
  24. በጭነት ተሸከከርካሪ በተፈቀደው አግባብ ካልሆነ በስተቀር በተሸከርካሪው የውጭ አካል ሰውን ያሳፈረ 1500 ብር እና በጫነው በእያንዳንዱ ትርፍ ለተጫነ ሰው ተጨማሪ 100 ብር ይቀጣል። 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top