የደቡብ ፖሊስ ኮሌጅ ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ጋር ተቀላቀለ

1 Yr Ago 1140
የደቡብ ፖሊስ ኮሌጅ ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ጋር ተቀላቀለ

የደቡብ ፖሊስ ኮሌጅ አዲስ የተደራጁትን ክልሎች ለማስተናገድ እንዲቻል ወደ ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ እንዲካተት በተወሰነው ውሳኔ መሠረት  ዛሬ የተቋም ርክክብ አካሂዷል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ባደረጉት ንግግር፤ ኢትዮጵያ በተለይም የደቡብ ክልል የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት መዳረሻ በመሆኑ ሰላሙ እንዲጠበቅ የፖሊስ ኃይሉን ማጠናከር ወሳኝ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

ሰላምን ከሚጠብቁ ተቋማት አንዱ የሆነውን የፖሊስ ኃይል በተሻለ መልኩ በፖሊሳዊ ዲሲፕሊንና የቴክኖሎጂ አቅሙ የዳበረ እንዲሆን የማሰልጠኛ ተቋማት ድርሻ ከፍተኛ መሆኑም ነው የገለጹት።

የደቡብ ፖሊስ ኮሌጅን ወደ ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ እንዲቀላቀል መወሰኑ የፖሊስን አንድነት የሚያሳይ መሆኑን ጠቅሰው ፤ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ የተሰጠውን ከባድ ኃላፊነት ተረክቦ በተሰጠው እምነት ልክ እንዲሰራ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል መስፍን አበበ በበኩላቸው፤ እንደ ሀገር የተጀመረውን ፈጣን ዕድገት በተሳካ መልክ ማካሄድ የሚቻለው ሀገራዊ እሳቤን በመያዝ እንደሆነ አንስተው የክልልና የፌደራል ፀጥታ ተቋማት ተቀናጅተው መስራት ያሰፈልጋል ብለዋል።

ለሀገራዊ ልማት የሚጠበቅብንን ድርሻ ለመወጣት የተሰጠንን አደራ በሚገባ ጠብቀን፤  ከዚህ ቀደም ከሚሠጠው አገልግሎት በተሻለ አግባብ መስጠት እንዲንችል ተደራጅተን እንሠራለን ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top