ማዕከላዊ ኢትዮጵያ በሚል ለሚደራጀው ክልል ማሻሻያ ተደርጎበት የተዘጋጀው ሕገ-መንግስት ጸደቀ

1 Yr Ago 2570
ማዕከላዊ ኢትዮጵያ በሚል ለሚደራጀው ክልል ማሻሻያ ተደርጎበት የተዘጋጀው ሕገ-መንግስት ጸደቀ

የደቡብ ክልል ምክር ቤትና የብሄረሰቦች ምክር ቤት ዛሬ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስቸኳይ የጋራ ጉባኤ ተካሂዷል። 

በጉባኤው በነባሩ የደቡብ ክልል ሕገ-መንግስት ማሻሻያ ተደርጎበት የተዘጋጀ የ "ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል" ህገ መንግስት ለምክር ቤቱ አባላት ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ በአብላጫ ድምጽ መፅደቁን ኢዜአ ዘግቧል። 

የጋራ ምክር ቤቱ ነገ በሚያካሂደው ጉባኤ የ"ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል" የአስፈጻሚ አባላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣ ረቂቅ ሰነድ ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ ተመላክቷል። 

እንዲሁም የሚቀርቡለትን ልዩ ልዩ ሹመቶችን ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የወጣው መርሃ-ግብር አመላክቷል።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top