“ኢትዮጵያውያን አረንጓዴ ታሪክ ሠርታችኋል” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

1 ዓመት በፊት 289
“ኢትዮጵያውያን አረንጓዴ ታሪክ ሠርታችኋል” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የምስጋና መልዕክት

500 ሚልዮን ዛፎችን በመትከል የራሳችንን ሪከርድ እንድንሰብር የቀረበውን ጥሪ ተቀብላችሁ የወጣችሁ ሁሉ ምስጋና ይገባችኋል። ኢትዮጵያውያን አረንጓዴ ታሪክ ሠርታችኋል። አረንጓዴ ታሪክ ጽፋችኋል ሲሉ ገለጹ።

የተዛባ አየር፣ የተራቆተ ምድር ለትውልድ አናወርስም ብላችሁ፤ ጎሕ ሳይቀድ ወደ ተራሮችና ሸለቆዎች፣ ወደ ሜዳዎችና ሸንተረሮች ተሠማርታችሁ 566 ሚልዮን ዛፎች ተክላችኋል። ሪከርዳችሁን ሰብራችኋል ብለዋል።

በሁሉም ክልሎች፣ ዞኖችና ወረዳዎች ዛፎች ተተክለዋል። ከ9 ሺ በላይ የተለዩ ቦታዎች ተዘጋጅተው ነበር። ከ3600 በላይ የሚዲያ ባለሞያዎች በመላ ሀገሪቱ ተሠማርተው ነበር። የቴሌና የግብርና ባለሞያዎች የመረጃ አያያዙ ዘመናዊ እንዲሆን ሠርተዋል።

የአዲስ አበባ ታክሲዎች ነጻ ትራንስፖርት ለችግኝ ተካዮች ተሰጥተዋል። ሕጻናት፣ እናቶች፣ አባቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ በነቂስ ወጥተው ተክለዋል። ኢትዮጵያውያን ዛሬ አረንጓዴ ታሪክ ተሠርተዋል።

ኢትዮጵያውያን ከተባበርን የማንሰብረው ሪከርድ የለም ሲሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top