የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንት ፋሊፔ ኒዪሲ አዲስ አበባ ገቡ

1 Yr Ago
የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንት ፋሊፔ ኒዪሲ አዲስ አበባ ገቡ

የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንት ፋሊፔ ኒዪሲ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሀመድ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ጨምሮ ሌሎ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ዛሬ ማለዳም በ36ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ የኬኒያ ፕሬዚደንት ዊሊያም ሩቶን፣ የሞሪታኒያ ፕሬዝዳንት ሙሀመድ ኦልድ ጋውዛኒን፣ የኬፕቬርዴ ፕሬዚደንት ጆሴ ማሪያ ፔሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ከትናንት በፊትም የሴራሊዮን፣ የኮሞሮስ፣ የቡሩንዲ፣ የታንዛኒያ፣ የሩዋንዳ፣ የሌሴቶ፣ የናይጀሪያ ፕሬዝዳንቶችን ጨምሮ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፣ የዑጋንዳና የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንቶች እና የሌሎች የአፍሪካ አገራት መሪዎች መዲናዋ ገብተዋል።

36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤም በመጪው ቅዳሜና እሁድ “የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራን ማፋጠን” በሚል መሪ ሃሳብ ይካሄዳል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top