ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በመተማመን ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ለመፍጠር እየወሰዷቸው ያሉ ርምጃዎች የሚደነቁ ናቸው - የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት

18 Hrs Ago 94
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በመተማመን ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ለመፍጠር እየወሰዷቸው ያሉ ርምጃዎች የሚደነቁ ናቸው - የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በመተማመን ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ለመፍጠር እየወሰዷቸው ያሉ ርምጃዎች የሚደነቁ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የአፍሪካ ጉዳዮች ተመራማሪ ሚፍታህ መሀመድ ገልጸዋል፡፡

ተመራማሪው በፍጥነት ተለዋዋጭ በሆነው የዓለም የፖለቲካ ሥርዓት ውስጥ ብሔራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ በሳል የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡  

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በአንካራ ያደረጉት ስምምነት በቀጣናው የነበረውን ውጥረት ያረገበ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡ 

ስምምነቱ ሻክሮ የነበረው የሀገራቱን ግንኙነት ለማደስ ትልቅ ምዕራፍ መክፈቱንም ለEBC DOTSTREAM ተናግረዋል፡፡ 

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በመተማመን ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ለመፍጠር እየወሰዷቸው ያሉ ርምጃዎችም የሚደነቁ መሆናቸውን አጽዕኖት ሰጥተዋል፡፡

የኢትዮጵያ በሳል የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ በሀገራቱ መካከል የነበረውን አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ማስቻሉንም አውስተዋል፡፡

በሀገራቱ መካከል የሚፈጸሙ ስምምነቶች ቋሚ እና አስተማማኝ እንዲሆኑ በመርሕ ላይ የተመሰረቱ ሊሆኑ እንደሚገባም አበክረዋል፡፡ 

የአፍሪካ ቀንድ ወሳኝ ጂኦፖለቲካዊ ቦታ መሆኑን የሚገልጹት ተመራማሪው፤ ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላም እና ትብብር ጉልህ ሚና እንዳላት ተናግረዋል፡፡

አክለውም የሀገሪቱ የህልውና ጉዳይ የሆነውን የባህር በር ፍላጎት ለማሳካት በጋራ ተጠቃሚነት እሳቤ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች ይበልጥ ሊጎለብቱ እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡

በአፎሚያ ክበበው


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top