በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 164 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

17 Hrs Ago 81
በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 164 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ የነበሩ እና ለአደጋ የተጋለጡ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

በዛሬው ዕለት ወደ ሃገራቸው የተመለሱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 164 ነው።

ተመለሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን፣ የፌዴራል ፖሊሲ ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዬች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ሲራጅ ረሽድ አቀባባል አድርገውላቸዋል።

በተለያዩ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዜጎችን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ብሄራዊ ግብረኃይል ተቋቋሙ በመስራት ላይ ይገኛል።

በዚሁ ግብረሃይል አስተባባሪነት በሊባኖስ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ደህንነታቸው ለአደጋ የተጋለጠ ዜጎችን የመመለሱ ስራ እየተከናወነ ሲሆን፤ እስካሁን 758 ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሃገር ቤት መመለስ መቻሉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top