የኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ትርፋማነት መግባቱ ተገለጸ

22 Hrs Ago 90
የኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ትርፋማነት መግባቱ ተገለጸ
የኢትዮ-ጂቡት ባቡር መስመር በ2024 የመጨረሻው ሩብ ዓመት ወደ ትርፋማነት መግባቱን የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) ገለጹ፡፡
 
አሁን እያሳየ ያለው ትርፋማነት ድርጅቱ ወደ ሥራ ከገባበት ጊዜ አንስቶ ከፍተኛው መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጠቅሰው፤ ይህ ስኬት ኩባንያውን አትራፊ ለማድረግ የተያዘው የሦስት ዓመት ስትራቴጂያዊ እቅድ እንደሚሳካ ማሳያ ነው ብለዋል።
 
"ለዚህ ስኬት አስተዋፅኦ ላበረከቱ የኢትዮጵያም ሆነ የጂቡቲ ወገኖች ምስጋናዬን አቀርባለሁ" ያሉት ታከለ ኡማ (ኢ/ር)፤ በዚህ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ለመድረስ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ታማኝ ሠራተኞች ልዩ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
 
ይህ ወሳኝ ጅማሮ ሲበሰር ለኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር ምርጡ ጊዜ ገና እንደሚመጣ መገንዘብ አስፈላጊ መሆኑን አንስተው፤ ለጠንካራ ትርፋማነት መሰረት በመጣሉ ቀጣይ ጉዞው ወደ ላቀ ስኬት መሆኑን በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸውባጋሩት መልዕክት አስታውቀዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top