ሰላም የተረጋገጠባት ሀገር ለመገንባት የምክር ቤት አባላት በሰላም ጉዳይ ከህዝብ ጋር ተቀራርበው መስራት አለባቸው፡- ምክትል አፈ ጉባኤ ሎሚ በዶ

19 Hrs Ago 74
ሰላም የተረጋገጠባት ሀገር ለመገንባት የምክር ቤት አባላት በሰላም ጉዳይ ከህዝብ ጋር ተቀራርበው መስራት አለባቸው፡- ምክትል አፈ ጉባኤ ሎሚ በዶ
ሰላም የተረጋገጠባት ሀገር ለመገንባት የምክር ቤት አባላት በሰላም ጉዳይ ከህዝብ ጋር ተቀራርበው መስራት እንዳለባቸው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሎሚ በዶ አስገነዘቡ።
 
የህዝብ ተወካዮች፣ የፌደሬሽን እንዲሁም የክልል እና ከተማ አስተዳድር ምክር ቤቶች በጋራ በመሆን "ምክር ቤቶቻችን ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታችን" በሚል መሪ ሀሳብ በአዳማ እየመከሩ ነው።
 
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሎሚ በዶ፤ያጋጠሙንን ሁለንተናዊ ስብራቶች በመጠገን ሰላም የተረጋገጠባት ሀገር ልንገነባ ይገባል ብለዋል።
 
ምክትል አፈ ጉባዔዋ ቀደምት ሀገር ኢትዮጵያ ሰላሟ የተረጋገጠ እና ኅብረ ብሔራዊ አንድነቷ የተጠበቀ እንዲሆን የምክር ቤት አባላት ከወከላቸው ህዝብ ጋር ተቀራርበው መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል።
 
የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ለዘላቂ ሰላም ጠንካራ ተቋማት ያስፈልጋሉ ያሉ ሲሆን፣ የምክር ቤት አባላትም ተቋማት ላይ የሚያደርጉትን የክትትል እና የቁጥጥር ስራ ሊያጠናክሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።
 
ምክር ቤቶች ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመሆን በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን በቅርበት እየሰሩ ስለመሆኑም ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
 
በመስከረም ቸርነት
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top