የተጀመሩ የልማት ስራዎች በማህበረሰቡ ተሳትፎ ጥሩ ውጤት እየተገኘባቸው ነው፡- የጌዴኦ ዞን አስተዳደር

1 Mon Ago 141
የተጀመሩ የልማት ስራዎች በማህበረሰቡ ተሳትፎ ጥሩ ውጤት እየተገኘባቸው ነው፡- የጌዴኦ ዞን አስተዳደር
የተጀመሩ የልማት ስራዎች በማህበረሰቡ ተሳትፎ ጥሩ ውጤት እየተገኘባቸው እንደሚገኝ የጌዴኦ ዞን አስተዳደር አስታውቋል።
 
በዞኑ ዲላ ከተማ ከ552 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የተለያዩ ኘሮጀክቶች በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል።
 
የትምህርት ተቋሟት ማስፋፊያ ግንባታ፣ የፖሊስ ማዕከል፣ በመናኸሪያ የደንበኞች አገልግሎት መስጫ ማዕከልን ጨምሮ በከፊል የተጠናቀቁ የኮሪደር ልማት ስራዎች ዛሬ ከተመረቁት መካከል ይገኙበታል።
 
የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) በዞኑ በማህበረሰብ ድጋፍ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች የልማት ክፍተቶችን በመሙላት ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛል ብለዋል።
 
ባለፈው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከገጠር እስከ ከተማ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የልማት ስራዎች በመንግሥት እና ማህበረሰብ ተሳትፎ ማከናወን መቻሉ ተገልጿል።
 
በሚካኤል ገዙ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top