የጅቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ለመሆን ሶስት እጩዎች ከፍተኛ ፉክክር ሲያደርጉ ቆይተዋል።
በዚህም በስራ ላይ ያሉትን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት ለመተካት በተካሄደው ምርጫ የጅቡቲው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ 33 ድምፅ በማግኘት ምርጫውን አሸንፈዋል።
በ7 ዙር በተካሄደው ምርጫ እጩ ሆነው የቀረቡት የቀድሞ የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ 21 ድምፅ በማግኘት ሁለተኛ ሆነዋል።
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ወርቅነህ ገበየሁ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው፤ ማህሙድ አሊ ዩሱፍ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አለዎ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
በመታሰቢያ ደረጀ