በሰላም እና ደህንነት ላይ የሚመክረው አህጉር አቀፍ የአፍሪካ የሰላም ጉባዔ "የበለጸገና ሰላማዊ አፍሪካን እንገንባ" በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
በመድረኩ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀሥላሴ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዷለም፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረዳት ዋና ፀሐፊ እና በኢትዮጵያ የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ዶክተር ራሚዝ አላክባሮቭ፣ የአፍሪካ ሕብረት የፖለቲካ ፣ የሰላም እና ደህንነት ጉዳዮች ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዴዎዬ፣የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ የዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ተቋማት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የአፍሪካ የሰላም ስብሰባ ሰላም የሰፈነባት፣ የበለጸገችና የለማች አፍሪካን እውን ለማድረግ በጋራ የሚመክሩበት መድረክ ነው።
ኢትዮጵያ ለዓለምና ለቀጣናው ሰላም ከኮሪያ ዘመቻ እስከ ሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ያበረከተችው አስተዋጽኦ እንደሚቀርብ ኢዜአ ዘግቧል።
በአፍሪካ ሰላምና ብልጽግናን ለማረጋገጥ ትብብር ለቀጣናው ትስስር ያለው ፋይዳ በሩዋንዳ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ቪንሰንት ቢሩታ (ዶ/ር) ይቀርባል።