በመንግስት ከሙኒኬሽን አገልግሎት አስተባባሪነት ከተለያዩ መገናሃኛ ብዙሃን የተወጣጡ የጋዘጠኞች ቡደን በኦሮሚያ ክልል አርሲ እና ባሌ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በተጨባጭ ሁኔታ መሬት ላይ ተግባራዊ እየሆነ ያለዉን የግብርና ስራዎችን ምልከታ አድርጓል፡፡
በባሌና አርሲ ዞኖች ምልከታ በተደረገባቸዉ የተለያዩ ወረዳዎች በሁሉም ዘርፍ የአርሶ አደሩን ህይወት ለመለወጥ በመንግሰት ተቀርፆ ተግባራዊ እየ ሆነ ካለዉ አዳዲስ ኢኒሼቲቮች መካከል የግብርና ልማት ስራዎች አንዱ ሲሆን፣ እየተከናወኑ ባሉ ተግባራት ተጨባጭ ለውጦች መምጣታቸውን መመልከት ተችሏል፡፡
በክላስተር እየለማ የስንዴ ምርት፣ በዘመናዊ የእንስሳት እርባታ፣ ዘመናዊ ቀፎን ተጠቅሞ በንብ አርባታ ላይ የስራ እድል የተፈጠረላቸዉ ወጣቶች፣ እንዲሁም በቤተሰብ ደረጃ በሌማት ቱሩፋት ሥራ ኑሯቸውን እየቀየሩ መሆኑን መመልከት ተችሏል፡፡
የመንግሰት ከሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ በሚዲያ ቅኝቱ ወቅት በሰጡት ማብራሪያ ግብርናን በተመለከት የመግሥት ዋናው ትኩረት የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥና በቂ ምርት አምርተው ለገበያ ማቅረብ ሲሆን እቅዱ በተጨባጭ ተግባራዊ መሆኑን፣ እንዲሁም ሀገሪቱ ያላትን እምቅ አቅሞች በመለየት ወደ ተግባር በመግባት በአጭር ጊዜ አስደናቂ ለውጦች መመዝገባቸውን አንስተዋል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአርሶ እና አርብቶ አደሩን የሕይወት ዜይቤ እንዲ ቀየርና ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ግብርና ከባህላዊ ዘዴ ወደ ዘመናዊነት እንዲሸጋገር በማድረግ ላይ የተከናወኑ ስራዎች አበረታች ዉጤቶችን እያስመዘገቡ እንደምገኙ ተናግረዋል፡፡
ይህንን ተግባር ለማሳካትም መንግሰት ለአርሶ አደሩ ከሙያዊ እገዛ ጀምሮ እስከ ማካናይዤሽንና የግብርና ግባዓት አቅርቦት _ ትራክቴር፤ ኮምባይነርና የሌሎች ግብአቶች አቅርቦትን በማመቻቸት ዘርፈ ብዙ ድጋፎች መደረጋቸውን ገልፀዋል፡፡
ይህንን ተከትሎም መንግስት በአርሶ አድር ማሳ ላይ የሚመረት ምርት በብዛት፤ጥራትና ፍጥነት እንዲመረት የመንግሰት ቁልፍ ተግባር በመሆኑ በክላስተር ፤ ጥምር ግብርና እና ሌማት ቱሩፋት ላይ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች አመላክች መሆናቸዉን አብራርተዋል፡፡
እንደ ሚኒስትር ዴኤታዉ ገለፃ እንደ ሀገር መንግሰት የኢኮኖሚዉ ተግባር ዉጤታማ እንዲሆን አራቱ የኢኮኖሚ ግቦች ብሎ የለያቸዉ ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፤ ኤክስፖርትን ማሳድግ፤ከዉጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ዉስጥ ምርት መተካት እና የስራ እድል ፋጠራ እንደ ሆኑ ገልፀዋል፡፡
በኦሮሚያ ክልል በባሌ እና አርሲ ዞን በተጨባጭ ሁኔታ ሁለንተናዉ የበተሰብ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ተግባራዊ እየሆኑ ያሉ አዲስ ኢኒሼቲቭ የሆነዉ የግብርና ዘርፍ ስንዴን በክላስተር ማምረት፤ በቢራ ገብስ፤ በሌማት ቱሩፋት እና ስራ እድል ፈጠራ ላይ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች ትልቅ ለውጥ ማምጣታቸውና ለሁሉም ልማት ስራዎች ወሳኝ የሆነ በዞኖቹ ሰላም በመረጋገጡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡