በሊባኖስ በተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ ኢትዮጵያውያን ላይ ችግር እንዳይደርስ በቅርበት እየተከታተልኩ ነው - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

21 Days Ago 150
በሊባኖስ በተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ ኢትዮጵያውያን ላይ ችግር እንዳይደርስ በቅርበት እየተከታተልኩ ነው - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሊባኖስ የተፈጠረውን ወቅታዊ ሁኔታ ተከትሎ በኢትዮጵያውን ዜጎች ደኀንነት ላይ ችግር እንዳይደርስ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ገለጸ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ዙሪያ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን የዋናው መሥሪያ ቤት የሥራ ኃላፊዎች እና በሊባኖስ ቤይሩት ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት አመራሮች እና ዲፕሎማቶች ጋር በወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ተወያይተዋል።

በውይይቱ በሊባኖስ የተፈጠረው ውጥረት በአገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎች እና ቤይሩት በሚገኘው ቆንስላ ጀኔራል ጽ/ቤት ውስጥ የሚሠሩ ዲፕሎማቶች እና ሠራተኞች ደኀንነት ላይ ችግር እንዳይደርስ ለማድረግ እየተከናወኑ ባሉ ዝግጅቶች ላይ ያተኮረ ነው።

በዚህ ወቅት ሚኒስትር ዴኤታዋ፤ መንግሥት ለዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ በሰጠው ቅድሚያ ትኩረት መሠረት ለተፈጠረው ሁኔታ ልዩ ትኩረት በመሥጠት ክትትል እያደረገ መሆኑን መግለፃቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

በቀጣይም መንግሥት ለዜጎች በሚደረገው ክትትል እና ድጋፍ ዙሪያ በዋናው መስሪያ ቤት፣ በቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት እንዲሁም በኢትዮጵያውያን ማኀበረሰብ አደረጃጀቶች በኩል መረጃ እንደሚያደርስም ሚኒስትር ዴኤታዋ አስታውቀዋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top