የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር

2 Mons Ago 396
የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር

የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር  በሽታ ምንድነው? የሚለውን እንዲመልሱልን የማህፀን እና ፅንስ ሐኪም እንዲሁም የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ ከሆኑት ዶክተር ህዝቅኤል ጴጥሮስ ጋር ኢቢሲ ሳይበር ቆይታ አድርጓል። 

እንደ ዶክተር ህዝቅኤል ማብራሪያ፥ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ማለት ማህፀን ላይ የሚከሰት ያልተለመደ የሰውነት ህዋሳት መብዛት ነው። 

ካንሰር በሰውነታችን ውስጥ ያሉ ሴሎች ከቁጥጥር ውጪ በሆነ መልኩ መባዛትና ማደግ ሲጀምሩ እና ወደ ሌላ የሰውነታችን ክፍሎች ሲሰራጩ የሚከሰት በሽታ ነው ብለዋል። 

በሽታው በዓለም አቀፍ ደረጃ በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር ዓይነቶች ከጡት ካንስር ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ነው። 

የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር በሽታ "ሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ" በሚባል ረቂቅ ተዋህስ የሚከሰት በሽታ እንደሆነም ዶክተር ህዝቅኤል ይገልጻሉ። 

በቫይረሱ የተጠቁ አብዛኛው ሰዎች በበሽታው መያዛቸያን ሳያውቁ እና ምልክቱ ሳይታይባቸው ከ10 እስከ 20 ዓመት ሊኖሩ ይችላሉ። 

የበሽታው መነሻ መንስዔ በለጋ ዕድሜ የግብረ ስጋ ግንኑነት መጀመር፣ ከብዙ ወንዶች ጋር የግብረስጋ ግንኙነት መፈጸም፣ ከብዙ ሴቶች የወሲብ ግንኙነት ካለው ወንድ ጋር የግብረስጋ ግንኙነት መፈጸም፣ በአባለዘር በሽታ መጠቃት፣ የሰውነት በሽታ መከላከል አቅም መዳከም እና ሌሎች ተዛማጅ ምክንያቶች እንደሆኑም ዶክተር ህዝቅኤል አብራርተዋል። 

ምልክቶቹ፦

  • ያልተለመደ የደም መፍሰስ
  • የጀርባ፣ የባትና የዳሌ ሕመም፣ ድካም
  • የምግብ ፍላጎት መቀነስ
  • ከሴቷ ብልት የሚወጣ ሮዝ፣ ቡናማ ወይም የደም ቀለም ያለው፣ ሽታ ያለው ፈሳሽ የመሳሰሉ ምልክቶችን የማየት ዕድል ስለመኖሩ ባለሙያው አንስተዋል። 

የማህፀን በር ካንሰር በሽታን በክትባት መከላከል እንደሚቻል የሕክምና ባለሙያው ያስረዳሉ። 

መከላከያው፦

  • ታማኝነትና አንድ ለአንድ መወሰን፣
  • በለጋ ዕድሜ ከግብረስጋ ግንኙነት መታቀብ፣
  • (የግብረስጋ ግንኑነት ለጀመሩ ሴቶች) መደበኛ የሆነ የማህፀን ምርመራ ማድረግ እና ኮንዶምን በአግባቡ መጠቀም የማህፀን በር ካንሰርን ለመከላከል አስፈላጊ እንደሆነም ዶክተር ህዝቅኤል ጴጥሮስ አመላክተዋል። 

በሜሮን ንብረት


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top