በፓሪስ ኦሎምፒክ የምልመላ፣ የቴክኒክ እና የስነ ልቦና ችግሮች በመሰረታዊነት ተስተውለዋል - የስፖርት ሳይንስ ተመራማሪ

2 Mons Ago 338
በፓሪስ ኦሎምፒክ የምልመላ፣ የቴክኒክ እና የስነ ልቦና ችግሮች በመሰረታዊነት ተስተውለዋል - የስፖርት ሳይንስ ተመራማሪ

በፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ላይ የኢትዮጵያ አትሌትክስ የምልመላ፣ የቴክኒክ እና የስነ ልቦና ችግሮች በመሰረታዊነት ይስተዋልበት እንደነበር የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ ዶ/ር ደምስ ጋሹ ገለጹ፡፡

ኦሎምፒክ ለኢትዮጵያ ውጤት የማግኘትና የማጣት ጉዳይ ሳይሆን የሀገር ክብር፣ የአንድነትና የታሪክ ጉዳይ ነው ያሉት ተመራማሪው፤ በፓሪስ ኦሎምፒክ በአትሌትክሱ ያመጣነው ውጤት እንደ ታሪካችን ውለን ማደር አለመቻላችን ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

በረጅም ርቀት ዓለም የሚያውቀን ህዝቦች ሆነን፣ በርጅም ርቀት የተለየ ብቃት ያላቸውን አትሌቶችን በማፍራት የደመቀ ታሪክ ይዘን ነገር ግን ውጤት እየራቀን መጥቷል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከአበበ ቢቂላ ጀምሮ እስከ ታምራት ቶላ ድረስ በረጅም ርቀት ትልቅ ታሪክ ያላት መሆኑን ያነሱት ዶ/ር ደምስ ጋሹ፤ ይህን የአሸናፊነት ውርስ ማስቀጠል አለመቻሉን ተናግረዋል፡፡

ከኢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረጉት ዶ/ር ደምስ፤ በኦሎምፒክ አመራሩ በኩል ለአትሌቶች እምብዛም ትኩረት ያልተሰጠበት፣ ውሳኔዎች ሁሉ ሰው እጅ እንዲወድቁ የሆነበት ሁኔታ ብዙ ነገሮችን አበላሽቷል ብለዋል፡፡

የአትሌቶች ምልመላ ላይ የአሰልጣኞች ችግር እንደነበረ የሚያሳየው፣ አትሌት ታምራት ቶላ በወቅታዊ ብቃቱ ታይቶ ቀርቶ ነበረ ነገር ግን ተወዳድሮ ውጤታማ መሆን መቻሉ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

የፓሪስ ኦሎምፒክ ላይ የኢትዮጵያ አትሌትክስ የምልመላ፣ የቴክኒክና የስነ ልቦና ችግሮች በመሰረታዊነት ይስተዋልበት ነበር ብለዋል፡፡

ከታክቲክና የቴክኔክ ስልጠና ባሻገር የአካል ብቃት፣ የስነ ልቦና ጋር የተያያዙ ጉዳዮች መሟላትና መፈተሸ ይኖርባቸዋል ሲለም አንስተዋል፡፡

በኦሎምፒክ ውድድር ለኢትዮጵያ የሚገባት ወርቅ ነው ያሉት ዶ/ር ደምስ ጋሹ፤ ተሳትፎ ብቻውን በቂ ነው የሚለውን ሀሳብ እንደማይቀበሉት ተናግረዋል፡፡

በመሃመድ ፊጣሞ

 


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top