የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ለቱሪዝም ዘርፉ ትልቅ ተስፋ የሰነቀ ዘመን ተሻጋሪ የሀገር ሃብት ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

1 Mon Ago 298
የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ለቱሪዝም ዘርፉ ትልቅ ተስፋ የሰነቀ ዘመን ተሻጋሪ የሀገር ሃብት ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ለቱሪዝም ዘርፉ ትልቅ ተስፋ የሰነቀ ዘመን ተሻጋሪ የሀገር ሃብት መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በትላንትናው እለት ተመርቋል።

በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ለቱሪዝም ዘርፉ ትልቅ ተስፋ የሰነቀ ዘመን ተሻጋሪ የሀገር ሃብት መሆኑን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ እምቅና አስደናቂ የቱሪዝም ሃብቶች ቢኖሩም በመሰረተ ልማት እጥረት ለጎብኝዎች እምብዛም ተደራሽ ሳይሆኑ መቆየታቸውን አስታውሰው አሁን ላይ በስፋትና በጥራት እየለሙ መሆኑን ተናግረዋል።

መንግስት ለቱሪዝም ልማት በሰጠው ትኩረት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሃሳብ አመንጪነት ዜጎችን በማስተባበር በርካታ ፕሮጀክቶች ተገንብተው እየተጠናቀቁ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በዚህ ረገድ የጎርጎራና አካባቢው አስደናቂ ስፍራ ለዘመናት ልማት ርቆት ውበቱና ሃብቱ ሳይገለጥ የቆየ መሆኑን አስታውሰው አሁን ላይ ለቱሪስቶች ምቹ መዝናኛ ሆኖ መሰራቱን ገልጸዋል።

በታሪካዊው ስፍራ ላይ በዘመናዊ መልኩ የተገነባው የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ሁነኛ የቱሪስት መዳረሻ ለመሆን ዝግጁ ሆኗል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በአማራ ክልል የተለያዩ መሰረተ ልማቶች፣ የቱሪዝም ልማትና ኢንዱስትሪዎች እየተስፋፉ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top