ኢትዮጵያ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራች ነው፡- በለጠ ሞላ (ዶ/ር)

16 Days Ago 239
ኢትዮጵያ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራች ነው፡- በለጠ ሞላ  (ዶ/ር)
ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት ከአጋር አካላት ጋር በትብብር እየሰራች መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለጹ።
 
ሚኒስትሩ የዓለም አቀፍ የቴሌ ኮሙኒኬሽን ህብረት የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ኢማኑኤል ምናሴ (ዶ/ር) በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
 
ውይይቱ በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ትግበራ ላይ በትብብር መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው።
 
ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት መፋጠንና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን እውን ማድረግ ወሳኝ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፥ በዲጂታል ኢኮኖሚው ላይ በትብብር በመስራት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት እና ባለቤትነትን ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ገልጸዋል።
 
ኢትዮጵያን ወደ ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ እድገት ለማሸጋገር በሚያስችለው የዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ላይ እምርታዊ እድገት ለማምጣት የሚያስችሉ የትብብር ስራዎችን በማጠናከር የዲጂታል ኢኮኖሚውን እድገት ለማሳካት እንደሚሰራ አመላክዋል።
 
ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በዲጂታል ዘርፍ ሁሉን አቀፍ ስራ እያከናወነች መሆኑን ተናግረዋል።
 
ዓለም አቀፉ የቴሌኮም ህብረት በኩል የሚወጡት የሀገራት የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽንስ ቴክኖሎጂ ደረጃ ፍትሃዊነት እና የሀገራትን ወቅታዊ ስራዎች ከግምት ውስጥ ያስገቡ መሆን እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
 
የዓለም አቀፍ የቴሌ ኮሙኒኬሽን ህብረት የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር ኢማኑኤል ምናሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ኢትዮጵያ በዲጂታል ዘርፍ የያዘችው ግብ እንዲሳካ ተቋማቸው በትብብር እንደሚሰራ አመልክተዋል።
 
ህብረቱ የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ትግበራን ለማሳለጥ እየተከናወኑ ላሉ ስራዎች ድጋፍ የማድረግ ፍላጎት እንዳለው መናገራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።
 
በቀጣይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያን አስመልክቶ የሚወጡ መረጃዎች አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top