ሩሲያ ለአሜሪካ የኒውክሌር ሙከራዎች ተመሳሳይ ምላሽ ትሰጣለች - ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን

1 Mon Ago
ሩሲያ ለአሜሪካ የኒውክሌር ሙከራዎች ተመሳሳይ ምላሽ ትሰጣለች - ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አሜሪካ የኒውክሌር ሙከራዎችን የምታደርግ ከሆነ ሩሲያም ተመሳሳይ ምላሽ ትሰጣለች ሲሉ ተናገሩ፡፡

ፕሬዝዳንቱ ከሀገራቸው መገናኛ ብዙሃን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ አሜሪካ የኒውክሌር መሳሪያ የምትሞክር ከሆነ ሀገራቸው ተመሳሳዩን ለማድረግ እንደምትገደድ ገልፀዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በንግግራቸው፤ ሀገራቸው ከሌሎች ሀገራት በቴክኖሎጂው የበላይነት እንዳላት ጠቅሰው፤ በዚህም አሜሪካ ለምታደርጋቸው ማናቸውም ሙከራዎች ሩሲያ በእጥፉ ምላሽ እንደምትሰጥ አመልክተዋል፡፡

የአሜሪካን ጦረኞች በዩክሬን መመልከት እንደማይፈልጉ የገለፁት ፕሬዝዳንቱ፤ የአሜሪካ ወታደሮች በዩክሬን ምድር የሚገኙ ከሆነ በሞስኮ በኩል ጣልቃ ገብ ተደርገው እንደሚቆጠሩም ነው የተናገሩት፡፡

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሀገራቸው የኒውክሌር ጦርነት ዝግጁ መሆኗንም በቃለ-ምልልሱ ላይ ጠቅሰዋል፡፡

በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ጋር ተያይዞም ምንም እንኳ ውጥረት ቢኖርም በዩክሬን ምድር የኒውክሌር መሳሪያ ማሰማራት አስፈላጊ ሆኖ አለመገኘቱን ፕሬዝዳንቱ መናገራቸውን ቲአርቲ ወርልድ ዘግቧል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top