በህንድ ተደርምሶ የተዘጋ ዋሻ ውስጥ የነበሩ 41 ሰራተኞች ከ17 ቀናት ቁፋሮ በኋላ ወጡ

10 Mons Ago 251
በህንድ ተደርምሶ የተዘጋ ዋሻ ውስጥ የነበሩ 41 ሰራተኞች ከ17 ቀናት ቁፋሮ በኋላ ወጡ
 
ሰራተኞቹን ለማውጣት 4.5 ኪሎ ሜትር ያህል ቁፋሮ የተደረገ ሲሆን የመጨረሻው የቁፋሮ ስራ አስቸጋሪ በመሆኑ በእጅ መደረጉ ተገልጿል።
90 ሳንቲ ሜትር ስፋት ባለው ትቦ ከ17 ቀናት የዋሻ ቆይታ በኋላ መውጣት የቻሉት የግንባታ ሰራተኞች ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን ከመካከላቸው አንድም የተጎዳ ሰው የለም ነው የተባለው።
ሲልክያራ የተባለው ሰው ሰራሽ የትራንስፖርት መተላለፊያ ዋሻ ባለፈው ህዳር 1 ከተደረመሰ በኋላ በውስጡ የነበሩ ሰራተኞችን ለማውጣት ከፍተኛ ጥረት በህንድ መንግስት ሲደረግ ነበር።
የህንድ ፕሬዚዳንት ድሩፓዲ ሙርሙ በቀድሞ ቲውተር ባሁኑ ኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ በሰራተኞቹ በህይወት መውጣት የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው የነፍስ አድን ሰራተኞችን ያላሰለሰ ጥረት አድንቀዋል።
ለ17 ቀናት በዋሻ ውስጥ የቆዩቱን ሰራተኞች በአካባቢው ሆነው ሲጠባበቁ የነበሩት ቤተሰብ እና ጓደኞቻቸው መውጣታቸውን ተከትሎ ደስታቸውን መግለጻቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top