ጤና ሚኒስቴር ለሁሉም ክልሎችና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ለወሊድ እና ድንገተኛ አደጋ አገልግሎት የሚውሉ 370 አምቡላንሶችን አስረክቧል።
የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ዛሬ ማለዳ ለከተማ አስተዳደሮቹ እና ለክልሎች የጤና ቢሮያ ኃላፊዎች አስረክበዋል።
ሚኒስትሯ በዚህ ወቅት እንደገለጹት፤ አምቡላንሶቹ በጤናው ዘርፍ የተቀመጡ ግቦችንን ለማሳካት ሚናቸው የጎላ ነው።
ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ከ3 ሺህ በላይ አምቡላንሶች ለከተማ አስተዳደሮችና ለክልሎች እንዲተላለፉ መደረጉንም አስታውሰዋል።
በዚህም በተለይ በእናቶች ሞት እና በድንገተኛ አደጋ ቅነሳ ዙሪያ አመርቂ ውጤት እንደተመዘገበበት ማንሳታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።