ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ያስገነባውን የድንገተኛ ህክምና ማዕከል በከፊል አገልግሎት አስጀመረ

2 Days Ago 165
ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ያስገነባውን የድንገተኛ ህክምና ማዕከል በከፊል አገልግሎት አስጀመረ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ያስገነባውን የድንገተኛ ህክምና ማዕከል በከፊል አገልግሎት አስጀምሯል።

በማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይም የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ የትምህርት ሚኒስትርና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

በዚሁ ወቅት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር)፤ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን የህክምና ልህቀት ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በከፊል ስራ የጀመረው የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የድንገተኛ ህክምና ማዕከል የድንገተኛ ህክምና አገልግሎቱን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሻሽልም ገልጸዋል።

ከዚህ ባሻገር ማዕከሉ ኢትዮጵያን የህክምና ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ትርጉም ያለው ድርሻ እንደሚኖረውም አመልክተዋል።

ማዕከሉን በሙሉ አቅም ወደ ስራ ለማስገባት ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያስፈልግ ሲሆን የባለድርሻ አካላት ርብርብም ወሳኝ እንደሆነ ተጠቁሟል።

ሆስፒታሉ በዓመት ከ14ሺህ እስከ 15ሺህ ለሚደርሱ ዜጎች የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት እየሰጠ መቆየቱ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top