ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ሕልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የኀዘን መልዕክት፤ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በማረፋቸው የተሰማኝን ኀዘን እገልጻለሁ ብለዋል።
አቶ ቡልቻ በሚችሉት ሁሉ ሀገራቸውንና አፍሪካን ያገለገሉ፣ በአቋማቸው ጽኑ፣ ሕዝቦችን ለማቀራረብ የተጉ፣ እውነት ነው ብለው ያመኑትን የትምና መቼም የሚናገሩ እንደነበሩ ጠቅሰዋል።
እንዲህ ዓይነት ብርቱ ሽማግሌዎችን ማጣት ጉዳቱ ለሀገር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ፈጣሪ ነፍሳቸውን ይቀበላት ብለዋል።