በደቡብ ኮሪያ 181 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ በነበረ አውሮፕላን ላይ በደረሰው አደጋ የሟቾች ቁጥር 179 መድረሱ ተገልጿል።
አውሮፕላኑ 175 መንገደኞችን እና 6 የሚሆኑ የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ ከታይላንድ ባንኮክ ወደ ደቡብ ኮሪያ ሙአን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ ሲሞክር መከስከሱ ተጠቅሷል።
ከተከሰከሰው አውሮፕላን ውስጥ የአደጋ ሠራተኞች ሁለት ሰዎችን በሕይወት ማግኘታቸው ተመላክቷል፡፡
ደቡብ ኮሪያ በተከሰተው የአውሮፕላን አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ሰዎች የሰባት ቀናት ብሔራዊ ሀዘን ማወጇም ተጠቅሷል።
የአውሮፕላኑ የበረራ መረጃ መመዝገቢያ ሳጥን (ብላክ ቦክስ) መገኙቱና የአደጋ መንስኤውን ለማጣራት ምርመራ መቀጠሉም ተነግሯል።
የሟች ቤተሰቦች በአውሮፕላን ማረፊያው አዳራሽ ውስጥ ተሰብስበው አስከሬን እስኪታወቅ እየጠበቁ ሲሆን፤ ህይወታቸው ካለፉ ሰዎች መካከል የተወሰኑት በጣት አሻራቸው ብቻ መለየታቸው ተጠቁሟል።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ አደጋ የደረሰበት ይህ አውሮፕላን ጀጁ የተባለ አየር መንገድ ንብረት የሆነ ቦይንግ 737-800 መሆኑ ተጠቅሷል፡፡