በዶናልድ ትራምፕ ሆቴል መግቢያ በር ላይ በደረሰ የሳይበርትራክ መኪና ፍንዳታ 1 ሰው ሞቶ 7 ቆሰሉ

2 Days Ago 195
በዶናልድ ትራምፕ ሆቴል መግቢያ በር ላይ በደረሰ የሳይበርትራክ መኪና ፍንዳታ 1 ሰው ሞቶ 7 ቆሰሉ

በነዳጅ እና ሪችት የተሞላ ሳይበርትራክ መኪና ላስቬጋስ፣ ኔቫዳ በሚገኘው የዶናልድ ትራምፕ ሆቴል መግቢያ በር ላይ መፈንዳቱ ተገልጿል። 

በፍንዳታው የመኪናው አሽከርካሪ ሞቶ ሌሎች 7 ሰዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል። 

የቴስላ ስሪት የሆነው ሳይበርትራክ መኪና ከፍንዳታው ከ2 ሰዓታት በፊት ጀምሮ በሆቴሉ መግቢያ በር ላይ ቆሞ እንደቆየ ተገልጿል። 

ጥቃቱ ከአዲስ ተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወይም ከቴስላ ባለቤት ኢሎን መስክ ጋር ተያያዥነት እንዳለው በመጣራት ላይ መሆኑን ኤፍ.ቢ.አይ አስታውቋል። 

ፍንዳታው በኒው ኦርሊንስ ከተማ ከተፈፀመው ጥቃት ጋር የተቀናጀ ስለመሆኑም እያጣራን ነው ሲሉ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ተናግረዋል። 

ከኔቫዳው አደጋ አስቀድሞ በኒው ኦርሊንስ ከተማ፣ ፍሬንች ኳርተር በሚባለው አካባቢ አንድ አሽከርካሪ በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ መኪና በመንዳት ባደረሰው ጥቃት እስካሁን የሟቾች ቁጥር 15 ደርሷል። 

በአፎሚያ ክበበው


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top