የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ1ኛ ዙር ከ12ኛ እስከ 19ኛ ሳምንት መርሃ ግብር በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ከነገ ታህሳስ 25/2017 ዓ.ም እስከ የካቲት 03/2017 ዓ.ም ይካሄዳል።
ነገ አርብ ከቀኑ 9፡00 ጀምሮ አርባ ምንጭ፣ ከሲዳማ ቡና፤ ከ12፡00 ጀምሮ ፋሲል ከነማ፣ ከሀዋሳ ከተማ ጋር እንደሚጫወቱ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ይፋ ያደረገው መረጃ ያመለክታል።
የፊታችን ቅዳሜ ታህሳስ 26/2017 ዓ.ም ከ9፡00 ጀምሮ ባህር ዳር፣ ከድሬዳዋ ከተማ፤ ከ12፡00 ጀምሮ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር እንደሚጫወቱ የወጣው መርሃ ግብር ያሳያል።
የፊታችን እሁድ ታህሳስ 27/2017 ዓ.ም ከ9፡00 ጀምሮ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣ ከአዳማ ከተማ፤ ከ12፡00 ጀምሮ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ከመቐለ 70 እንደርታ ይጫወታሉ።
የፊታችን ሰኞ ታህሳስ 28/2017 ዓ.ም ደግሞ ከ9፡00 ጀምሮ ኢትዮጵያ መድን፣ ከስሑል ሽረ፤ ከ12፡00 ከ9፡00 ጀምሮ መቻል፣ ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።
በላሉ ኢታላ