በሶማሊ ክልል ጎዴ ከተማ እየተካሄደ ያለው ለውጥ አበረታች መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት፤ "ከዓመት በፊት ወደ ጎዴ መጥቼ ነበር፤ ከዚያ ወዲህ እየተካሄደ ያለው ለውጥ አበረታች ነው" ብለዋል፡፡
በጽኑ ሃሳብ ማተኮር ያለብን በልማት ላይ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህ መንገድ ለእድሎች በር የሚከፍት፣ የሕይወት ደረጃን የሚያሻሻልና ማኅበረሰብን የሚያሻግር ጎዳና ነው ሲሉ ጠቅሰዋል።
በምዕራብ ጎዴ የመስኖ ፕሮጀክት በተለይ ደስታ ተስምቶኛልም ነዉ ያሉት።
በአንድ ወቅት ገላጣ የነበረው በረሃማ መሬት በመስኖ አሁን ታርሶ በተስፋ ሰጪ አቅም የሰሊጥ፣ ስንዴ፣ በቆሎ አዝርዕት ምርት እና በተለያዩ የፍራፍሬ ምርቶች የተሞላ ስፍራ ሆኗል ሲሉም ገልጸዋል።