በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ማካሄድ ለምን አስፈለገ?

21 Hrs Ago 48
በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ማካሄድ ለምን አስፈለገ?
ሀገራዊ ምክክር በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲካሄድ ሁለት መነሻ ምክንያቶች አሉ።
 
👉የመጀመሪያው በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ የሀሳብ መሪዎች እንዲሁም የሕብረተሰብ ክፍሎች መካከል እጅግ መሠረታዊ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሀሳብ ልዩነት እና አለመግባባት መኖሩ ነው።
 
👉ሁለተኛው ምክንያት ለዘመናት ሲንከባለሉ የመጡ ውስጣዊ ችግሮችን በውይይት ለመፍታት የሚያስችል የፖለቲካ ባሕል ለማዳበር እና ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ምቹ መደላድል መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ ነው።
 
በአጠቃላይ ከሌሎች ሀገራት ልምድ በመነሳትና የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ በማጥናት በኢትዮጵያ የሚደረገው ሀገራዊ ምክክር የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ያበረታታል።
 
ስለሆነም የሚስተዋሉትን ሰፍፊና ዘርፈ ብዙ ልዩነቶች ለመፍታት አካታች የሆኑ የህዝብ ምክክሮችን ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ በሀገራችንም ውስጥ ይህንን ለማስጀመር ወደ ስራ ተገብቷል።
 
ከዚህም ባሻገር ምክክሩ የሀገራችንን ጥቅም ማስቀደምን እና ሀገር በቀል እውቀቶችን መጠቀምን እንደ መሠረታዊ መርሆቹ አድርጎ ስለሚወስድ ሂደቱን ከውጭ ተፅዕኖ ነፃ እንዲሆን ያደርገዋል።
 
ምንጭ ፡- የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top