የአፍሪካ ወጣቶችን ለ2063 አጀንዳ መሳካት ያላቸውን አቅም ለመጠቀም ተቋማዊ አሰራሮች ሊተገበሩ ይገባል - በአፍሪካ ህብረት የወጣቶች ልዩ መልእክተኛ

2 Mons Ago
የአፍሪካ ወጣቶችን ለ2063 አጀንዳ መሳካት ያላቸውን አቅም ለመጠቀም ተቋማዊ አሰራሮች ሊተገበሩ ይገባል - በአፍሪካ ህብረት የወጣቶች ልዩ መልእክተኛ

የአፍሪካ ወጣቶችን ለ2063 አጀንዳ መሳካት ያላቸውን አቅም አሟጦ ለመጠቀም የሚያስችሉ ተቋማዊ አሰራሮች ሊተገበሩ እንደሚገባ በአፍሪካ ህብረት የወጣቶች ልዩ መልእክተኛ ቺዶ ምፔምባ ገለፁ።

ልዩ መልእክተኛዋ በአፍሪካ ህብረት መግለጫ በሰጡበት ወቅት፤ በህብረቱ ራእይ ቁጥር ስድስት መሰረት ልማትን በወጣቶች ማረጋገጥ ያትታል ያሉ ሲሆን፤ ለዚህም መረጋገጥ ወጣቶችን ማሳተፍና ተጠቃሚ ማድረግ በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ ገልፀዋል።

ከሰላም እና ፀጥታ ጋር በተያያዘ ወጣቱን የሰላሙ አካል በማድረግ እንዲሁም ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የውሳኔው አካል በማድረግ የሰላሙ ጠባቂ ለማድረግ በህብረቱ አባል ሃገራት መተግበር ያለበት መሆኑንም ልዩ መልእክተኛዋ አንስተዋል።

የአፍሪካ ወጣት ትልቁ ፈተና ዛሬም ስራ አጥነት በመሆኑ ህብረቱም ሆነ አባል ሃገራት ከዚህና ከተያያዥ ጉዳዮች ጋር በጋራ ከመስራት ባለፈ ፖለቲካዊ ቁርጠኝነታቸውን ሊያረጋግጡ እንደሚገባ ልዩ መልእክተኛዋ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጠቁመዋል።

በኮሰን ብርሃኑ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top