ብሔራዊ መታወቂያ እ.ኤ.አ እስከ 2025 ለሁሉም ዜጎች ይዳረሳል

12 Mons Ago 623
ብሔራዊ መታወቂያ እ.ኤ.አ እስከ 2025 ለሁሉም ዜጎች ይዳረሳል

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እና ብሔራዊ መታወቂያ በጋራ መስራት በሚያስችላቸው አግባብ ላይ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ሁለቱ ተቋማት ስምምነቱን ያደረጉት ሁሉም ዜጎች የብሔራዊ መታወቂያ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል እንደሆነ ነው የተገለፀው።

ዲጂታል መታወቂያ ማንነትን በትክክል በመግለፅ ማጭበርበርን እና ሙስናን ለመከላከል እንደሚያግዝ የዲጀታል ሲቪል ሰርቪስ መረጃ ማደራጃ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ብሩክ ይርጋ ተናግረዋል።

ዲጂታል መታወቂያ እያደገ የመጣውን ዲጂታል የንግድ ስርዓት ይበልጥ ለማሳደግም አስተዋጽኦው የጎላ ነው ተብሏል።

እስካሁን ሶስት ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች የብሔራዊ መታወቂያ ተጠቃሚ ለመሆን ተመዝግበዋል።

የብሔራዊ መታወቂያ ቴክኒካል ዳይሬክተር ኢዮብ አለሙ በበኩላቸው፥ ዲጂታል መታወቂያ እ.ኤ.አ እስከ 2025 ድረስ በመላ ሀገሪቱ ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ ይደረጋል ብለዋል።

ብሔራዊ መታወቂያ ለማደል እስካሁን የአስፈላጊ ቁሳቁስ እና የአገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች አለመሟላት ችግር እንደነበርም ተጠቁሟል።

አሁን ላይ የአስፈላጊ ቁሳቁስ ግዥ የተፈፀመ በመሆኑና አስፈላጊ የሰው ኃይል የማሟላት ስራም እየተጠናቀቀ በመሆኑ በቀጣይ ሶስት ዓመታት ሀሉንም ዜጎች የብሔራዊ መታወቂያ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራም ተገልጿል።

በአስማረ ብርሃኑ


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top